ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካና የደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ልምምድን “ከእንግዲህ አልታገስም” ብላለች
ሰሜን ኮሪያ በትናትናው አልት ብቻ 23 ሚሰዔሎችን መተኮሷ ተነግሯል።
አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ባሳለፍነው ሰኞ በአይነቱ ግዙፍ የተባለ የአየር ኃይል ወታደራዊ ልምመድ መጀመራቸው ይታወቃል ።
ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካና የደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ልምምድን “ከእንግዲህ አልታገስም” ያለች ሲሆን፤ ለዚህም የተለያዩ የማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች።
በትናንትናው እለትም ሰሜን ኮሪያ ቢያንስ 23 ሚሳዔሎችን ተኩሳለች የተባለ ሲሆን፤ ከእነዚህም አንዱ ደቡብ ኮሪያ የባህር ጠረፍ ላይ መውደቁ ተነግሯል።
በተጨማሪም አንድ የአህጉር ቋራጭ ሚሳዔል ኢላማው ስፍራ ሳይደርስ በመሃል ሊወድቅ ይችላል የተባለ ሲሆን፤ በርካታ ጃፓናውያንም ራሳቸውን እንዲጠብቁ እና መከላከያ ምሽጎች ውስጥ እንዲሆኑ የማስጠንቀቂያ መልእክት ደርሷቸዋል።
ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ የሰሜን ኮሪያን እርምጃ ኃላፊነት የጎደለው ሲሉ መኮነናቸውንም ሮይተርስ ዘግቧል።
ሰሜን ኮሪያ በትናትናው እለትም ለአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ኤር ኃይል የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ምላሽ ለመስጠብ ተበማለም 100 ምፎችን መተኮሷ ይታወሳል።
አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የጀመሩት የአየር ኃይል የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሰሜን ኮሪያን ያስቆጣ ሲሆን፤ ባወጣችው የማስጠንቀቂያ መግለጫ በአሜሪካ እና በደቡብ ኮሪያ መካከል የሚደረገውን መጠነ ሰፊ የአየር ልምምድ “ግጭት ቀስቃሽ” ነው ብላለች።
ሀገራቱ ከድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ እርምጃ እንደመትወስድም ዛቻ አዘል መልእክት አስተላልፋች።
ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ በቅርቡ በአወዛጋቢው የባህር ድንበር አከባቢ ማስጠንቀቂያ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸው ተከትሎ በሁለቱም ኮሪያዎች ግጭት ሊፈጠር እንደሚችል ሲዘገብ ቆይቷል።
እስካሁን በሁለቱም ኮሪያዎች መካካል ጦርነት መደረጉ የሚያመላክቱ ሪፖርቶች ባይኖሩም በኮሪያ ባረ ሰላጤ ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ ያለው የባህር ድንበር ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ደህንነት ስጋት ምንጭ መሆኑ ይታወቃል።