ሰሜን ኮሪያ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ሚሳዔል አስወነጨፈች
የፒንግያን የትናትናው እለት የሚሳዔል ማስወንጨፍ በ5 ቀናት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ነው
ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካ ም/ፕሬዝዳንት ደቡብ ኮሪያን ለቀው በወጡ በሰዓታ ውስጥ ነው ሚሳዔሎችን የተኮሰችው
ሰሜን ኮሪያ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዝ ሚሳዔሎቸን ማስወንጨፏ ተስመቷል።
ፒዮንግ ያንግ በደቡብ ኮሪያ ጉብኝት ላይ የነበሩት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስ ሴኡልን ለቀው ከወጡ ከሰዓታት በኋላ ሚሳዔሎችን መተኮሷ ተነግሯል።
በዚህም ሰሜን ኮሪያ ሁለት የአጭር ርቀት ተወንጫፊ የባላስቲክ ሚሳዔሎችን ወደ ባህር የተኮሰች ሲሆን፤ ይህም በዚህ ሳምንት ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ ያካሄደችው የባላስቲክ ሚሳዔል ሙከራ ነው ተብሏል።
ሰሜን ኮሪያ በፒዮንግ ያግ ደቡባዊ አቅጣጫ ከሚገነው ሶንቹን ሁለት የአጭር ርቀት የባላስቲክ ሚሳዔሎችን እንደተኮሰች የደቡብ ኮሪያ ጦር አረጋግጧ።
የጃፓን ጦርም ሰሜን ኮሪያ የባላስቲክ ሚሳዔሎችን እንዳስወነጨፈች መመልከቱን አስታውቋል።
ሰሜን ኮሪያ ባሳለፍነው ማክሰኞ ሱናን ከሚባለው አካባቢ ሚሳዔሎች ማስንጨፏ የደቡብ ኮሪያና አሜሪካ የጋራ ወታደራዊ አዛዦች መግለጻቸው አይዘነጋም።
ሚሳዔሎቹ ወደ 360 ኪሎ ሜትር በመብረር 30 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ የመምዘግዘግ አቅም እንዳላቸው የገለጹት አዛዦቹ፤ የፒዮንጊያንግ ትንኮሳ የሴኡል-ዋሽንግተን ጥምረት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
"የሰሜን ኮሪያ ትንኮሳ የደቡብ ኮሪያ-አሜሪካን የመከላከል እና ምላሽ የመስጠት አቅም የበለጠ ያጎለብታል እንዲሁም እና ሰሜን ኮሪያ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የመገለሏ ጉዳይ የበለጠ የሚያጠናክር ነው" ሲሉም ተናግረዋል።