የሰሜን ኮሪያ የሳይበር ሰላዮች አዲስ ዘዴ ዘርግተው እየሰለሉ ነው ተባለ
ሰላዮቹ የውጭ ሀገር ሙህራንን በማታለል ምርምር እንዲጽፉላቸው እያደረጉ ነው ተብሏል
ዘመቻው ሰሜን ኮሪያ ላይ የውጭ መንግስታት ፖሊሲን በመቅረጽ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ባለሞያዎች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ተነግሯል
አሜሪካዊ የውጭ ጉዳይ ተንታኝ ዳንኤል ዴፔትሪስ በጥቅምት ወር ከአንድ የምርምር ተቋም በተላከላቸው የኢሜል መልዕክት ፅሁፉ እንዲያዘጋጁ ተጠየቁ።
ነገር ግን ተንታኙ የተለመደው አይነት ስራ ሳይሆን የገጠማቸው የስለላ ስልትል ነበር።
መልዕክት ላኪው መረጃ የሚፈልግ የሰሜን ኮሪያ ሰላይ እንደነበር የሳይበር ደህንነት ተመራማሪዎች ተናግረዋል።
ሰላዩ እንደተለመደው ኮምፒውተሩን በመበርበር ሚስጥራዊነት ያለው መረጃ ከመስረቅ ይልቅ የአንድ የምርምር ተቋም ዳይሬክተር ነኝ በማለት፤ ዳንኤል ዴፔትሪስ በሰሜን ኮሪያ የደህንነት ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን ለመማወቅ መሞከሩን ተናግረዋል።
ኢሜሉ አዲስ እና ቀደም ሲል ሪፖርት ያልተደረገ የሰሜን ኮሪያ የመረጃ ጠለፊ ቡድን እንደሆነ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች ገልጸዋል። አምስት ኢላማ የተደረጉ ግለሰቦች እና ኢሜሎች በሮይተርስ ምርመራ ተደርጎባቸዋልም።
የጠለፋ ቡድኑ ከዚህ ቀደም ኢላማዎችን የይለፍ ቃሎችን ለመመንተፍ ኢሜሎችን ለረጅም ጊዜ እንደሚጠቀም ተገልጿል። አሁን ግን ተመራማሪዎችን ወይም ሌሎች ባለሙያዎችን አስተያየት እንዲሰጡ ወይም ሪፖርቶችን እንዲጽፉ በቀላሉ በመጠየቅ ላይ ናቸው።
ይህም ሚስጥራዊ መረጃን በቀላሉ ለማግኘት ያስችላቸዋል ነው የተባለው።
የማይክሮሶፍት የዛቻ ልህቀት ማዕከል ባልደረባ የሆኑት ጄምስ ኢሊዬት “አጥቂዎቹ በዚህ በጣም ቀላል በሆነ ዘዴ ብዙ ስኬት እያገኙ ነው” ብለዋል።
አዲሱ ዘዴ ባለፈው ጥር ወር ለመጀመሪያ ጊዜ ብቅ እንዳለም ተነግሯል። "አጥቂዎቹ የመረጃ ምንተፋ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ ቀይረዋል" ብለዋል።
ማዕከሉ "በርካታ" የሰሜን ኮሪያ ሰላዮችን ለይቻለሁም ብሏል።
ሰላዮቹ በዘመቻው ላይ ያነጣጠሩት ሙህራንና ተንታኞች በዓለም አቀፍ የህዝብ አስተያየት እና የውጭ መንግስታት ፖሊሲን በመቅረጽ በሰሜን ኮሪያ ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ እንደሆኑም ተነግሯል።
አጥቂዎቹ መረጃውን “ከፈረሱ አፍ” በቀጥታ እያገኙ ነው ተብሏል። “መረጃውንም መተርጎም አያስፈልጋቸውም። ምክንያቱም እነሱ በቀጥታ የሚያገኙት ከባለሙያው ነው" ሲሉ ጄምስ ኤሊዬት ተናግረዋል።ዘመቻው ሰሜን ኮሪያ ላይ የውጭ መንግስታት ፖሊሲን በመቅረጽ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ባለሞያዎች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ተነግሯል