ፖለቲካ
ሰሜን ኮሪያ በድጋማ የወታራዊ ስለላ ሳተላይት የማምጠቅ ሙከራ እንደምታደርግ ገለጸች
ሰሜን ኮሪያ የመጀመሪያዋን የወታደራዊ ሳተላይት ኦርቢት ላይ የማስቀመጥ ሙከራዋ ሳተላይቷ የተተኮሰችበት ሮኬት በኮሪያ ፔንዙላ በመከስከሱ ሳይሳካ ቀርቷል
ዮ ጆንግ በሺዎች የሚቆጠሩ ሳተላይቶች እያሉ ተመድ በሰሜን ኮሪያ የሳተላይት ሙከራ ላይ መስብሰቡ አግላይነቱን ያሳያል ሲሉ ከሰዋል
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እህት እና የገዥው ፖርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ኪም ዮ ጆንግ ሰሜን ኮሪያ የወታደራዊ የስለላ ሳተላይት በድጋሚ እንደምታመጥቅ ገልጸዋል።
ሰሜን ኮሪያ የመጀመሪያዋን የወታደራዊ ሳተላይት ኦርቢት ላይ የማስቀመጥ ሙከራዋ ሳተላይቷ የተተኮሰችበት ሮኬት በኮሪያ ፔንዙላ በመከስከሱ ሳይሳካ ቀርቷል።
ችግሩ የተከሰተው የሮኬቱ ሁለተኛ ደረጃ ወይም ስቴጅ አገልግሎት በማቆሙ ክብደት ተሸካሚው ክፍል ወደ ባህር ውስጥ እንዳወድቅ አድርጎታል።
"ቾሊና ዋን" የተሰኘችው ይህች ሳተላይት የወደቀችው በሞተር እና በነዳጅ ሲስተም ላይ ባጋጠማት ችግር እንደነበር ተገልጿል።
ዮ ጆንግ በሺዎች የሚቆጠሩ ሳተላይቶች እያሉ ተመድ በሰሜን ኮሪያ የሳተላይት ሙከራ ላይ መስብሰቡ አግላይነቱን ያሳያል ሲሉ ከሰዋል።
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ የተደቀነባትን ወታደራዊ ጥቃት ለመመከት ወታደራዊ የስለላ ሳተላይት እንዲኖራት መፈለጓ ተገቢ ነው ብለዋል ዮ ጆንግ።
ዮ ጆንግ ባለፈው አርብ እንደገለጹት ሁለተኛው ሙከራ የሚደረገው መቼ እንደሆነ ባይናገሩም የስላላ ሳተላይቱ በቅርቡ በኦርቢት ላይ እንደምትቀመጥ ተናግረዋል።