ሰሜን ኮሪያ፤ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያን ለማስጠንቀቅ ሚሳይል ማስቀንጨፏን አስታወቀች
ሚሳይሉ የተወነጨፈው በኮሪያ ልሳነ ምድር እና በጃፓን መካከል ወዳለው ባህር ላይ ነው
የ“ሁዋሶንግ-17” ሚሳይል አሜሪካን መምታት የሚችል አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል መሆኑ ይነገራል
ሰሜን ኮሪያ፤ የሁዋሶንግ-17 አህጉር አቋራጭ ሚሳይል (አይሲቢኤም) ማስቀንጨፏ አስታወቀች፡፡
ሀገሪቱ በትናንትነው እለት ከፒዮንግያንግ አውሮፕላን ማረፊያ ያስወነጨፈቸው ሚሳይል የጋራ ልምምድ በማካሄድ ላይ ላሉት ዋሽንግተን እና ሴኡል ጠንካራ ምላሽ ለመስጠት ነው ተብሏል፡፡
- ሰሜን ኮሪያ ማንኛውም የአሜሪካ ወታደራዊ እንቅቃሴ “የጦርነት አዋጅ” አድርጋ እንደምትቆጥር አሳሰበች
- የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሴት ልጅ የስፖርት ዝግጅት ላይ ታየች
ሚሳይሉ የተወነጨፈው በኮሪያ ልሳነ ምድር እና በጃፓን መካከል ወዳለው ባህር ላይ ነው፡፡
ፒዮንጊያንግ ሚሳይሉን ያስወነጨፈቸው የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ኒውክሌር የታጠቀችውን ሰሜን ኮሪያን ለመመከት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በሚመክረው የጃፓኑ መሪዎች ጉባኤ ለመገኘት ወደ ቶኪዮ ለመብረር ሰአታት ሲቀራቸው ነበርም ነው የተባለው፡፡
የሰሜን ኮሪያው ዜና አገልግሎት (ኬሲኤንኤ) እንደዘገበው "የስትራቴጂካዊ መሳሪያው (ሚሳይል) ሙከራ ሆን ብለው በኮሪያ ልሳነ ምድር ያለውን ውጥረት እያባባሱ ኃላፊነት የጎደላቸው እና ግድ የለሽ ወታደራዊ ስጋቶች እየፈጠሩ ላሉ ጠላቶች ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት እንደ መልካም አጋጣሚ ሆኖ ያገለግላል" ተብሏል፡፡
የሚሳይል ማስወንጨፍ ሙከራው ሲደረግ ኪም ከልጃቸው ጋር በስፋራው ተገኝተው ሲመለከቱ እንደነበርም ነው በሀገሪቱ የመንግስት ሚዲያዎች ያወጧቸው ፎቶዎች ሚያሳዩት፡፡
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የሚያካሂዱት ጋራ ወታደራዊ ልምምዱድ በኮሪያ ልሳነ ምድር ያለውን ውጥረት የሚያባብስ ነው ሲሉ ከሰዋል፡፡
"ጠላቶችን እንዲበረግጉ በማድረግ እና ጦርነትን በመግታት እንዲሁም ህዝባችን ሰላማዊ ህይወት ኖሮት ለሶሻሊስት ግንባታ የሚያደርገውን ትግል በአስተማማኝ ሁኔታ ዋስትና በመስጠት የኒውክሌር ጦርነትን መከላከል ያስፈልጋል" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የሰሜን ኮሪያ የባሊስቲክ ሚሳኤሎች በዋሽንግተን፣ ሴኡል እና ቶኪያ የተወገዙ ከመሆናቸው በተጨማሪ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተከለከሉ መሆናቸው ይታወቃል፡
“ሁዋሶንግ-17” የሚል ሲያሜ የተሰጠው ሚሳይል አሜሪከን መምታት የሚችል አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል መሆኑ ይነገራል፡፡
ሚሳይሉ 1,000 ኪሜ (621 ማይል) ርቀት የመምዘግዘግ አቅም አለውም ነው የተባለው፡፡
የደቡብ ኮሪያ እና የአሜሪካ ጦር ኃይሎች እየጨመረ የመጣውን የሰሜን ስጋት ለመከላከል ከ2017 ጀምሮ የጋራ ልምምድ ላይ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
አሁን ላይ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ለ11 ቀናት ሚቆይ ግዙፍ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ መጀመራቸውም እንዲሁ ይታወቃል፡፡