ሰሜን ኮሪያ ትንኮሳ ከተፈጸመባት ወታደራዊ ጥቃት እሰነዝራለሁ ስትል አስጠነቀቀች
ሰሜን ኮሪያ ከተቀናቃኟ ደቡብ ኮሪያ ጋር ወደሚያዋስናት ድንበር ለተከታታይ ሶስት ቀናት የከባድ መሳሪያ ተኩስ አሰምታለች
ሁለቱ ሀገራት አንደኛው ሌላኛቸውን በድንበር አካባቢ የተኩስ ልምምድ በማድረግ እየተካሰሱ ይገኛሉ
ሰሜን ኮሪያ ትንኮሳ ከተፈጸመባት ወታደራዊ ጥቃት እሰነዝራለሁ ስትል አስጠነቀቀች።
ሰሜን ኮሪያ ለሚደርስባት ማንኛውም ትንኮሳ ወዲያውኑ ወታደራዊ ምላሽ እንደምትሰነዝር የኪም ጆንግ ኡን እህት እና ዋነኛ አጋር ኪም ዮ ጆኔግ በዛሬው እለት ተናግረዋል።
ሰሜን ኮሪያ ከተቀናቃኟ ደቡብ ኮሪያ ጋር ወደሚያዋስናት ድንበር ለተከታታይ ሶስት ቀናት የከባድ መሳሪያ ተኩስ አሰምታለች።
ኪ ዮ ጆንግ ይህን ያሉት የደቡብ ኮሪያ መንግስት የሰሜን ኮሪያ ጦር አወዛጋቢ ወደሆነው የማሪታይም ድንበር 60 ጊዜ መተኮሷን ከገለጸ በኋላ ነው።
ሰሜን ኮሪያ ጦር የተኩስ ልምምዱን እያካሄደ ያለው በድንበሩ ትይዩ ስለሆነ ለደቡብ ኮሪያ ስጋት አይሆንም ብሏል።
የኪም ጆንግ ኡን እህት የሆኑት ኪ ም ዮ ጆንግ የኮሪያ ጦር መሳሪያውን አላቀባበለም ሲሉ ተናግረዋል።
ኪም አክለውም "ቀደም ሲል እንደታወጀው ጠላት ትንኮሳ የሚያደርግ ከሆነ ኮሪያን ፒፕልስ አርሚ(ኬፒኤ) ወዲያውኑ ጥቃት ይሰነዝራል" ብለዋል።
በሁለቱም በኩል በድንበር አካባቢ የሚደረጉ የተኩስ ልምምዶች በደቡብ ኮሪያ ውስጥ ባሉ ሁለት ደሴቶች ያሉ ነዋሪዎች እንዲለቁ ተደርገዋል።
ሁለቱ ሀገራት አንደኛው ሌላኛቸውን በድንበር አካባቢ የተኩስ ልምምድ በማድረግ እየተካሰሱ ይገኛሉ።
የደቡብ ኮሪያ እና የአጋሯ አሜሪካ የጦር መሳሪያ ልምምድ ያሰጋኛል የምትለው ሰሜን ኮሪያ ተደጋጋሚ የሚሳይል ሙከራ ማድረጓን ቀጥላበታለች።