የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ‘የማይበገር’ ሰራዊት እገነባለሁ አሉ
ኪም ጆን ኡን የአሜሪካ የጠላትነት ፖሊሲን ለመመከት ሰራዊቱን እንደሚገነቡ አስታውቀዋል
ሀገሪቱ የምትሰራቸው የጦር መሳሪያዎችም ራስን ለመከላከል መሆኑን ገልፀዋል
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የአሜሪካ የጠላትነት ፖሊሲን ለመመከት ‘የማይበገር’ ሰራዊት እንደሚገነቡ ማስታወቃቸው ተሰምቷል።
ኪም ጆንግ ኡን በፒንግያንግ 2021 የመከላከያ ኤግዚቢሽን ላይ ባደረጉት ንግግር ይህን ያሉ ሲሆን፤ ደቡብ ኮሪያ ሰራዊቷን እያጠናከረች መሆኑን በማሳት፤ ሰሜን ኮሪያ ከጎረቤቶቻን ጋር ጦርነት መግት አትፈልግም ብለዋል።
“እኛ ከማንም ጋር ስለ ጦርነት እየተወያየን አይደለም፤ ይልቁንም ጦርነትን እራሱን ለመከላከል እና የሀገሪቱን ብሄራዊ ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ነው የምንሰራው” ሲሉም ተናረዋል።
በሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ መካከል ውጥረት እንዲሰፍን አድርጋለች ሲሉም ኪም ጆንግ ኡን አሜሪካን መክሰሳቸውንም የሀገሪቱ መንግስተ መገናኛ ብዙሃ ዘግበዋል።
ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ ጠላት አይደለችም ብላ እንዳታምን የሚያደርግ “መሰረታዊ ባህሪ” የለም ሲሉም አስታውቀዋል።
ኪም ጆንግ ኡን አክለውም፤ ሰሜን ኮሪያ የምታካሂዳቸው የጦር መሳሪያ ግንባታዎች ራስን ለመከላከል እንጂ ጦርነትን ለመጀመር እንዳልሆነም ገልፀዋል።
ሰሜን ኮሪያ ሀገሪቱ በቅርቡ ረጅም ርቀት ተወንጫፊ የሆነ “ሀይፐርሶኒክ” ሚሳኤል መኩከራ ማደረጓ ይታወሳል።
ሚሳኤሎቹ 1 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት የመምዘግዘግ አቅም ያላቸው እንደሆኑም ኮሪያን ሴትንራል (KCNA) የተሰኘውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
አብዛኛውን የጃፓን መልክዓምድር የማዳረስ አቅም ያለው ነው የተባለለት የሚሳኤል ሙከራው፤ በሀገሪቱ ላይ የሚቃጣን ማንኛውንም ትንኮሳ ለመመከት እና የጠላት ኃይሎችን ወታደራዊ እንቅስቃሴ መቆጣጠር የሚያስችል መሆኑን ተመላክቷል።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በአመቱ መባቻ ላይ የሀገሪቱ ሳይንቲስቶች “በዓለም ላይ በጣም ኃይለኛ ከሆኑት የጦር መሣሪያዎች ሚሳይሎችን” እየሠሩ መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል።