ሰሜን ኮሪያ ከ2020 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ጎብኝዎችን ልትቀበል ነው
ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት ሀገሪቱ ከቻይና ጎብኝዎች ብቻ 175 ሚሊዮን ዶላር ታገኝ ነበር
በወረርሽኙ ወቅት ከባድ የሚባል የድንበር ቁጥጥር ካደረጉ ሀገራት ውስጥ ቀዳሚ ሰሜን ኮሪያ እስካሁን ድረስ ድንበሯን ለውጭ ጎብኝዎች ሙሉ በመሉ አልከተችም
ሰሜን ኮሪያ ከ2020 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ጎብኝዎችች ልትቀበል ነው።
ሰሜን ኮሪያ በኮኖና ወረርሽኝ ምክንያት ድንበሯን ከዘጋችበት ከፈረንጆቹ 2020 ወዲህ የሩሲያ ጎብኝዎች ቡድን ወደ ሰሜን ኮሪያ በመግባት የመጀመሪያው ለመሆን ተቃርዋል።
በወረርሽኙ ወቅት ከባድ የሚባል የድንበር ቁጥጥር ካደረጉ ሀገራት ውስጥ ቀዳሚ ሰሜን ኮሪያ እስካሁን ድረስ ድንበሯን ለውጭ ጎብኝዎች ሙሉ በመሉ ሳትከፍት ቆይታለች።
ይህ ጉዞ የተመቻቸው፣ ከሰሜን ኮሪያ ጋር የምትዋሰነው የሩሲያዋ የሩቅ ምስራቅ ፕሪሞርስካይ ክራይ ግዛት መሪ ባለፈው ወር በፒዮንግያንግ ውይይት ለማድረግ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ነው።
ሮይተርስ እንደዘገበው ጎብኝዎቹ ፒዮንግያንግን እና ስካይ ሪዞርትን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ለአራት ቀናት ይቆያሉ።
የሩሲያውያን ጉብኝት በተለየ ሁኔታ የተመቻቸ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ባለፈው መስከረም ወር በምስራቃዊ ሩሲያ በተገናኙበት ወቅት፣ በወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ቃል ገብተው ነበር።
ከሰሜን ኮሪያ ጋር በሚደረጉ የንግድ እንቅስቃሴዎች የተጣለው ተመድ የጸጥታው ምክርቤት ማዕቀብ፣ በቱሪዝም ላይ ተጽእኖ አላሳደረም።
ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት ሀገሪቱ ከቻይና ጎብኝዎች ብቻ 175 ሚሊዮን ዶላር ታገኝ ነበር።