ለሶስት ትውልድ የሰሜን ኮሪያ መሪዎች የፕሮፓጋንዳ ኃላፊ የነበሩት ኪም አረፉ
ኪም፣ የአሁኑ መሪ አባት ለሆኑት ኪም ጆንግ ኢል በተለየ መልኩ ቅርበት ነበራቸው ተብሏል
የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን "እስከ መጨረሻው ጊዜ በታማኝነት ላገለገሉት" ኪም ኪ ናም ሞት ሀዘናቸውን ገልጸዋል
ለሶስት ትውልድ የሰሜን ኮሪያ መሪዎች የፕሮፓጋንዳ ኃላፊ የነበሩት ኪም አረፉ።
የሰሜን ኮሪያን የሶስት ትውልድ መሪዎች ፖለቲካዊ ተቀባይነታቸውን በማጠናከር እና የፕሮፓጋንዳ ኃላፊ በመሆን ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ የነበሩት ኪም ኪ ናም ህይታቸው ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን "እስከ መጨረሻው ጊዜ በታማኝነት ላገለገሉት" ኪም ኪ ናም ሞት ሀዘናቸውን ገልጸዋል፤ ሸኝትም አድርገውላቸዋል።
ሮይተርስ የሀገሪቱን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ኬሲኤንኤ ጠቅሶ እንደዘገበው ኪም በተወለዱ በ94 አመታቸው ባለፈው ማክሰኞ አርፈዋል።
ሰሜን ኮሪያን በ1945 የመሰረቱት አብዮተኛ መሪ ጋር የደም ትስስር ያላቸው የኪም ቤተሰቦች መሪ እንዲሆኑ ተቀባይነታቸውን በማስቀጠል ታላቅ ሚና የነበራቸው እኝህ ኃላፊ፣ ታማኝ ከሚባሉት የባለስልጣናት ቡድን ውስጥ ነበሩ።
እንደዘገባው ከሆነ ኪም ሰሜን ኮሪያ በሁሉም ዘረፍ ጠንካራ የሆነች ሶሺያሊስት ሀገር እንድትሆን ጥረት አድርገዋል።
ከፒዮንግያንግ ጋር እርቅ እንዲደረግ በር የከፈቱት ፕሬዝደንት ኪም ዴ ጀንግ ከሞቱ በኋላ በቀብር ለመገኘት ወደ ደቡብ ኮሪያ ካቀኑት በጣም ጥቂት የሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት ልኡክ ውስጥ ተካተው ነበር።
ኪም በሰሜን ኮሪያ ፕሮፓጋንዳ ወደፊት የመጡት በ1966 ምክትል በመሆን ሲሆን የሀገሪቱ መስራች በሆነው ኪም ሁለተኛ ሰንግ የስልጣን ዘመን ደግሞ ዋና ኃላፊ ሆነዋል። ኪም በ2ዐ17 ጡረታ ወጥተዋል።
የሰሜን ኮሪያው ገዥ ፓርቲ 'ወርከርስ ፓርቲ' ፖለቲካዊ ስሪት ላይ ቁልፍ ሚና የነበራቸው ኪም፣ በፖሊሲ እና በሰራተኞች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደነበራቸው ተገልጿል።
ኪም፣ የአሁኑ መሪ አባት ለሆኑት ኪም ጆንግ ኢል በተለየ መልኩ ቅርበት ነበራቸው ተብሏል።