በአለምአቀፍ ንግድ ሚኒስትር የሚመራ የሰሜን ኮሪያ የልኡካን ቡድን በኢራን ያልተለመደ ይፋዊ ጉብኝት እያካሄደ ነው ተብሏል
የሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት በኢራን ያልተለመደ ይፋዊ ጉብኝት አደረጉ።
በአለምአቀፍ ንግድ ሚኒስትር የሚመራ የሰሜን ኮሪያ የልኡካን ቡድን በኢራን ያልተለመደ ይፋዊ ጉብኝት እያካሄደ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሰሜን ኮሪያ እና ኢራን ሚስጥራዊ የሆነ ወታደራዊ ግንኙነቶች እንዳላቸው ይገመታል።
ዘገባው የሰሜን ኮሪያን ቴሌሌቪዥን ኬሲኤንኤን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ በአለም አቀፍ የኢኮኖሚ ግንኙነት ሚኒስትር የን ጆንግ ሆ የሚመራው ልኡክ በትናንትናው እለት ከፒዮንግያንግ አቅንቷል።
ሰሜን ኮሪያ እና ኢራን ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ በባለስቲክ ሚሳይል ፕሮግራም ላይ በመተባበር፣ ምናልባትም የቴክኒክ ባለሙያዎቸን እና ምርት በመቀያየር ለረጅም ጊዜ ይጠረጠራሉ።
ከወራት በፊት ኢራን በዩክሬን እየተዋጋች ላለችው አጋሯ ሩሲያ ባለስቲክ ሚሳይል አሳልፋ ሰጥታለች የሚሉ ዘገባዎች ሲወጡ ነበር።
በተመሳሳይ ሰሜን ኮሪያም ለሩሲያ የከባድ መሳሪያ ተተኳሽ እና ሚሳይል በመስጠት መጠርጠሯ ይታወሳል።
ነገርግን ኢራንም ሆነች ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ አልሰጠንም ሲሉ አስተባብለዋል።
የኢራኑን የልኡክ ቡድን የሚመሩት የን ሀገሪቱ ከሶሪያ ጋር ባላት ግንኙነት ዙሪያ ሲሰሩ የነበሩ ናቸው ተብሏል።