በሀገራቱ መካከል ያለው ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሰሜን ኮሪያ አስታውቃለች
የሰሜን ኮሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪም ቶክ ሁን፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የደስታ መግለጫ ልከዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኪም ቶክ ሁን በደስታ መግለጫቸው፤ “ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት” ማለታቸውን የሰሜን ኮሪያ የዜና ማእከል መረጃ ያመለክታል።
- ፕሬዝዳንት ፑቲን ለጠ/ሚ ዐቢይ የደስታ መግለጫ ላኩ
- ሼህ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አልነሃያ እና ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ በስልክ መከሩ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በስልጣን ዘመንዎ ለሀገርዎ ልማት፣ ብልጽግና እና ሰላም እንዲመጣ በሚያደርጉት ጥረት ሁሉ ስኬትን እመኝሎታለሁ ካሉ በኋላ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ ወዳጅነት እና በትብብር የመስራት ፍላጎት እናጠናክራለን ብለዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ስኬትን የተመኙት የሰሜን ኮሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኪም ቶክ ሁን፤ በኢትዮጵያ ልማት፣ ብልጽግና እና መረጋጋት እንዲመጣ እንዲሰሩም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ ወዳጅነት እና በትብብር የመስራት ፍላጎት በመልካም ተሞክሮዎች ላይ በመመርኮዝ እያደገ እንደሚሄድም አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ የሰሜን ኮሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪይ ሰን ግዎንም ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የደስታ መግለጫ ልከዋል።
“በድጋሚ በመመረጥዎ የእንኳን ደስ አልዎት” ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅት ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ትልቅ ስኬትን እመኛለሁም ብለዋል።