የሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያዎች ባክሙት ላይ የዩክሬን ሲጠቀሟቸው ታይቷል
ዩክሬን የሰሜን ኮሪያን ሮኬቶችን በመጠቀም ሩሲያን ደበደበች።
የዩክሬን ወታደሮች "በወዳጅ" ሀገር ተይዘዋል ተላልፈው ተሰጥተዋል የተባሉ የሰሜን ኮሪያ ሮኬቶችን ሲጠቀሙ ተስተውለዋል ሲል ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል።
የዩክሬን መከላከያ ሚንስቴር መሳሪያዎቹ ከሩሲያውያን የተያዙ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ ታቀርባለች ስትል ክስ ሰንዝራለች። ነገር ግን ለክሱ ማስረጃ አላቀረበችም።
ሮይተርስ የሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያዎች በዩክሬን የጦር አውድማዎች ላይ በስፋት አልተስተዋሉም ብሏል።
ሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ በበኩላቸው የጦር መሳሪያ ግብይቶችን አለመፈጸማቸውን ተናግረዋል።
የሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያዎች ባክሙት ላይ በሶቪየት ዘመን በተሰራ ሮኬት ማስወንጨፊያ በዩክሬን ወታደሮች ጥቅም ላይ ሲውሉ መታየቱን ዘገባው ገልጿል።
መሳሪያዎቹ በማንና እንዴት ወደ ዩክሬን እጅ እንደገቡ የተባለ ነገር የለም።
የሩስያ መከላከያ ሚንስትር ሰርጌይ ሾይጉ የኮሪያ ጦርነት ያበቃበትን 70ኛ ዓመት ለማክበር በዚህ ሳምንት በፒዮንግያንግ ያልተለመደ ጉብኝት አድርገዋል።
ይህም የሞስኮ የመከላከያ ከፍተኛ ባለስልጣን ከ1991 የሶቪየት ህብረት መፍረስ በኋላ የመጀመሪያ ጉብኝት ነው።
በጉብኝቱ ወቅት ሾይጉ የተከለከሉትን የሰሜን ኮሪያ የባላስቲክ ሚሳይሎችን ከመሪው ኪም ጆንግ ኡን ጋር ተመልክተዋል።