የኤለን መስክ ኩባንያ ሙከራው ከተሳካ በግዙፉ ሮኬት ሰዎች እና ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ለማምጠቅ አቅዷል
የአለማችን ግዙፍ ሮኬት ዛሬ ወደ ህዋ እንደሚመጥቅ ተገልጿል።
“ሳታርሺፕ” የተሰኘው ሮኬት በአለማችን ሁለተኛው ባለጸጋ ኤለን መስክ ኩባንያ ስፔስኤክስ የተገነባ ነው።
120 ሜትር ይረዝማል የተባለው “ሳታርሺፕ” በሮኬቶች ታሪክ ግዙፉ ስለመሆኑ መነገሩን ሬውተርስ ዘግቧል።
ያለሰው የሚመጥቀው ሮኬት በቴክሳስ ይሞከራል ብሏል ኩባንያው ስፔስኤክስ።
የኩባንያው ባለቤት ኤለን መስክ ምናልባት የቴክኒክ ችግር ገጥሞ የማምጠቅ ሂደቱ ላይሳካ ስለሚችል ብዙ አትጠብቁ የሚል መልዕክቱን በትዊተር ገጹ ላይ አስተላልፏል።
ዛሬ የማይሳካ ከሆነ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ሙከራው እንደሚቀጥልም ነው ያስታወቀው።
ስፔስኤክስ በሽታርሺፕ ሮኬት ሰዎችን እና ሳተላይቶችን ወደ ጨረቃና ማርስ በፍጥነት ለማምጠቅ አቅዷል።
የሮኬት ማምጠቅ ሂደቱ 90 ደቂቃዎችን ይወስዳል ተብሏል።
የስፔስኤክስ “ስታርሺፕ” ሮኬት 33 ሞተሮች አሉት የተባለ ሲሆን፥ ዳግም ጥቅም ላይ ከሚውሉ ግብአቶች መሰራቱንም ኩባንያው ይፋ አድርጓል።