ሰሜን ኮሪያ ለአሜሪካና ደቡብ ኮሪያ የጦር ጄት ልምምድ የአጸፋ እርምጃ ወሰደች
ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካና ደቡብ ኮሪያ የጦር ጄት ልምምድን እንደ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ትመለከታለች
ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ጠዋት የባላስቲክ ምሳዔሎችን አስወንጭፋለች
ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የጦር ጄት ልምምድ ማድረጋቸውን ተከትሎ የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን አስታውቃለች።
አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ከሰሞኑ ኃይለኛ እና ፈጣን የሆኑ የጦር ጄቶችን ተጠቅመው የጋራ ወታራዊ ልምምድ ማድረጋቸው ይታወቃል።
ትናንት በተደረገው ልምምድ ላይም 2 የደቡብ ኮሪያ ኤፍ-35ኤ እና 2 የአሜሪካ ኤፍ-22 የጦር ጄቶች የጠሳተፉ ሲሆን፤ በደቡብ ኮሪያ የአየር ክልል ላይ የተቀናጀ የአየር ላይ ልምምዶች አድርገዋል።
የሁለቱን የጦር ጄት ልምምድ እንደ ብሄራዊ የደህንነት ስጋት የምትመለከተው ሰሜን ኮሪያም ለዚህ የሚሆን የአጸፋ ምላሽ መስጠቷ ታውቋል።
በዚህም ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ጠዋት ላይ የባላስቲክ ሚሳዔል የተኮሰች ሲሆን፤ ሚሳዔለሉ የተተኮሰውም ከሀገሪቱ ምስራቃዊ የባህር ጠረፍ ነው ተብሏል።
የደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ኃይል አዛዥ ሰሜን ኮሪያ የባላስቲክ ሚሳዔል መተኮሷን ያረጋገጡ ሲሆን፤ ምን ያክል ርቀት እንደተጓዘ እና የት እንደወደቀ ግን ዝርዝሩን አልተናገሩም።
ሰሜን ኮሪያ ከቅርብ ወራት ወዲህ ከአሜሪካ እና ከደቡብ ኮሪያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ እየሻረ መምጣቱን ተከትሎ ወታደራዊ አቅሟን እያሰፋች እና የተፋጠነ የጦር መሳሪያ ሙከራ እና ልምምድ በማድረግ ላይ ትገኛለች።
ባሳለፍነው ሳምንት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ተበገኙበት ሀገሪቱ አዲ የበርካታ ሮኬት ማስወንጨፊያ ስርዓት ሙከራ ማድረጓም ይታወሳል።