ሰሜን ኮሪያ የሦስትዮሽ ጉባኤውን ለመቃወም ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀች ነው- ደቡብ ኮሪያ
የአሜሪካ፣ የደቡብ ኮሪያ እና የጃፓንን የመሪዎች አርብ በአሜሪካ ይገናኛሉ
ፒዮንግያንግ እየተጠናከረ የመጣው የሦስቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብርን አደገኛ ብላለች
ሰሜን ኮሪያ የሦስትዮሽ ጉባኤውን ለመቃወም ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀች ነው- ደቡብ ኮሪያ
ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካ፣ የደቡብ ኮሪያ እና የጃፓንን የመሪዎች ስብሰባ በመቃወም አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳይል ልትተኩስ ወይም ሌላ ወታደራዊ እርምጃ ልትወስድ ትችላለች ተብሏል።
ይህን ያሳወቁት የሀገሪቱ የስለላ ድርጅትን ዋቢ በማድረግ የደቡብ ኮሪያ ህግ አውጪ ናቸው።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል እና ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ጋር አርብ በካምፕ ዴቪድ ይገናኛሉ።
ሀገራቱ የቻይና ቀጣናዊ ተጽዕኖ እያደገ በመምጣቱ የሰሜን ኮሪያ የኒውክሌርየር ስጋት መሀል ግንኙታቸውን ለማጠናከር ወጥነዋል።
ፒዮንግያንግ እየተጠናከረ የመጣው የሦስቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብርን "አደገኛ" ስትል ተችታለች።
ሀገሪቱ ትብብሩን "የኔቶን አምሳያ" በእስያ ለመፍጠር የሚሸረብ ሴረኝነት ነውም ብላዋለች።
ዩ ሳንግ ባም የተባሉት የደቡብ ኮሪያ የምክር ቤት አባል ፒዮንግያንግ የከሸፈባትን የስለላ ሳተላይት በድጋሚ ለመላክ ማቀዷንም ተናግረዋል።
ባለፈው ወር ሰሜናዊው ኮሪያና ሩሲያ ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።
ሦስቱ ሀገራት በፒዮንግያንግ እና ሞስኮ ትብብር ስጋት ውስጥ ገብተዋል።