ፕሬዝዳንት ኪም በደቡብ ኮሪያ ላይ የዘር ማጥፋት እንደሚያውጁ አስጠነቀቁ
ሰሜን ኮሪያ ከተተነኮሰች የኑክሌር አረሯን ከመጠቀም ወደኋላ እንደማትል አስታውቃለች
ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን የሰሜን ኮሪያ ጦር ሙሳሪያ ማምረቻ ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል
ፕሬዝዳንት ኪም በደቡብ ኮሪያ ላይ የዘር ማጥፋት እንደሚያውጁ አስጠነቀቁ።
የኮሪያ ልሳነ ምድር አሁንም ጸብ እንደሸተተው ሲሆን የሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን አሁንም በጎረቤታቸው ላይ ዝተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ደቡብ ኮሪያን የዘላለም ጠላት ነች በሚል የፈረጇት ሲሆን ትንኮሳ ከተፈጸመባቸው ጦራቸው ከምድረ ገጽ እንዲያጠፋት ትዕዛዝ መስጠታቸው ተገልጿል።
የሰሜን ኮሪያ ጦር መሳሪያ ማምረቻ ፋብሪካዎች በፕሬዝዳንቱ የተጎበኙ ሲሆን ጥቃት ከተፈጸመባቸው በደቡብ ኮሪያ ላይ የዘር ማጥፋት ወይም ጄኖሳይድ እንደሚፈጸም በይፋ ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንት ኪም ሀገራቸው ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት የገለጹ ሲሆን ትንኮሳ ከተፈጸመባቸው ግን ጦርነቱን የማስቆም ፍላጎት የለንም ሲሉም ተናግረዋል።
ይሁንና የደቡብ ኮሪያ ትንኮሳ ካሳየ ግን ሰሜን ኮሪያ እጇ ላይ ያሉትን የኑክሌር አረር እንደምትተኩስ ፕሬዝዳንት ገልጸዋል።
ሰሜን ኮሪያ በምርት ላይ ያሉት የጦር መሳሪያ ማምረቻ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ፕሬዝዳንቱ ሰራተኞችን አበረታተዋል።
ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ሰሜን ኮሪያ የተጣለባትን ማዕቀብ እየጣሰች ለሩሲያ ድጋፍ እያደረገች ነው ሲሉ መክሰሳቸው አይዘነጋም።
በፒዮንግያንግ እንደ ብሔራዊ ጠላት የምትታየው ደቡብ ኮሪያ በጎረቤቷ ወረራ ቢፈጸምብኝ በሚል ስጋት እውነተኛ የመልሶ ማጥቃት ልምምድ ከአንድ ወር በፊት ማድረጓ ይታወሳል።