ደቡብ ኮሪያ ጸረ-ፒዮንግያንግ በራሪ ወረቀቶችን መበተኗ አዲስ ውጥረት ቀሰቀሰ
ባለፈው ወር ሰሜን ኮሪያ ቆሻሻ የያዙ በሸዎች የሚቆጠሩ ፊኛዎችን ወደ ደቡብ መላኳን ተከትሎ በሴኡል እና ፒዮንግያንግ መካከል ያለው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር
ኪም እንደተናገሩት የደቡብ ኮሪያ መጥፎ ባህሪ የማይቀየር ከሆነ ፒዮንግያንግ የተለየ አካሄድ ልትከተል ትችላለች
ደቡብ ኮሪያ ጸረ-ፒዮንግያንግ በራሪ ወረቀቶችን መበተኗ አዲስ ውጥረት ተቀስቅሷል።
ደቡብ ኮሪያ፣ በሰሜን ኮሪያ ግዛት ውስጥ ጸረ-ፒዮንግያንግ የሆኑ መልእክቶችን የያዙ ወረቀቶች መቀተኗን ተከትሎ በኮሪያ ባህረ ሰላጤ አዲስ ውጥረት እንዲነግስ ምክንያት ሆኗል።
ደቡብ ኮሪያ ለዚህ ድርጊቷ "ከባድ ዋጋ ትከፍላለች" ስትል ሰሜን ኮሪያ ማስጠንቀቋን ሮይተርስ የሰሜን ኮሪያውን የመንግስት ሚዲያ ኬሲኤንን ጠቅሶ ዘግቧል።
ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እህት ኪም ዩ ጆንግ ጸረ-ፒዮንግያንግ በራሪ ወረቀቶችን የያዙ 29 ፊኛዎች በሰሜን ኮሪያ ውስጥ ድንበር አካባቢ መታየታቸውን እና በቦታው ያሉ ነዋሪዎችን ምቾት መንሳታቸውን ተናግረዋል።
ባለፈው ወር ሰሜን ኮሪያ ቆሻሻ የያዙ በሸዎች የሚቆጠሩ ፊኛዎችን ወደ ደቡብ መላኳን ተከትሎ በሴኡል እና ፒዮንግያንግ መካከል ያለው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። ፒዮንግያንግ ይህን ያደረገችው ሰሜን ኮሪያን በከዱ ሰዎች የተረነዘረባትን ዘመቻ እና ለአመታት ጸረ-ኪም አስተዳደር የሆኑ መልእክቶችን በጥብቅ በሚጠበቀው ድንበር አሾልከው የሚልኩትን የደቡብ ኮሪያ አክቲቪስቶች ለመቃወም ነው።
ኪም እንደተናገሩት የደቡብ ኮሪያ መጥፎ ባህሪ የማይቀየር ከሆነ ፒዮንግያንግ የተለየ አካሄድ ልትከተል ትችላለች።
"ሁኔታው ተቀባይነት ወደሌለው ደረጃ እያደገ ነው። በድጋሚ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ"ሲሉ ኪም በቴሌቪዥን በተላለፈው መግለጫ ተናግረዋል።
"አውዳሚ እና አስከፊ መልስ ይገጥማችኋል።"
ሰሜን ኮሪያ እና ደቡብ ኮሪያ ኃያላን ሀገራትን ከጎናቸው በማሰለፋቸው፣ ውጥረቱ እያየለ መጥቷል።
ደቡብ ኮሪያ በቀጣናው የአሜሪካ ዋነኛ አጋር ስትሆን ሰሜን ኮሪያም በቅርቡ ከሩሲያ ጋር ያላትን ወዳጅነት ወታደራዊ ስምምነት እስከመፈረም ድረስ ከፍ ማድረግ ችላለች።
ምዕራባውያን ሀገራት፣ ሰሜን ኮሪያ ሩሲያ በዩክሬን ለምታደርገው ጦርነት የጦር መሳሪያ እያቀረበች ነው የሚል ተደጋጋሚ ክስ ያቀርቡባታል። ሰሜን ኮሪያ ይህን ክስ ውድቅ አድርጋዋለች።