አሜሪካ ለዩክሬን እሰጣለሁ ያለቻቸው የረጅም ርቀት ሚሳይሎች የጦርነቱን ውጤት የመቀየር አቅማቸው ምን ያህል ነው?
በሁለት አመቱ ጦርነት ዩክሬን ከምዕራባውን በምታገኛቸው የጦር መሳርያዎች የሩሲያ ድንበር ውስጥ ጥቃት እንዳትፈጽም ተከልክላ ነበር
በዘንድሮው የኔቶ ጉባኤ አሜሪካ ከዩክሬን በተጨማሪ በጀርመን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎችን እተክላለሁ ብላለች
አሜሪካ ለዩክሬን እሰጣለሁ ያለቻቸው የረጅም ርቀት ሚሳይሎች የጦርነቱን ውጤት የመቀየር አቅማቸው ምን ያህል ነው?
ባሳለፍነው ሳምንት በተካሄደው የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አመታዊ ጉባኤ ላይ ኔቶ በሩሲያ ውስጥ በምዕራባውያን የጦር መሳርያዎች ጥቃት እንድትፈጽም ፈቃድ አግኝታለች፡፡
ከዚህ ባለፈም አሜሪካ እስከ 2026 በጀርመን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳይሎችን ለማስፈር ውሳኔ አሳልፋለች፡፡
ሁለት አመት በዘለቀው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ኬቭ በሞስኮ ድንበር ውስጥ በምዕራባውያን ሚሳይሎች እና ሌሎች የጦር መሳርያዎች ጥቃት እንዳትፈጽም እቀባ ተደርጎባት ቆይቷል፡፡
የጦርነት ተንታኞች ይህ እቀባ መነሳቱ የጦርነቱን ውጤት ምን ያህል ሊቀይረው ይችላል በሚል ትንታኔዎችን እያወጡ ይገኛሉ፡፡
የዩክሬን 148ኛ የመድፍ ብርጌድ አዛዥ “እስካሁን በነበረው ጦርነት የሩሲያ ጦር የምንዋጋው በራሳችን ግዛት ውስጥ ነበር፤ አሁን ግን ክልከላው በመነሳቱ ድንበር አቋራጭ ጥቃቶችን በመፈጸም የሩሲያን ጦር ግስጋሴ ለመግታት ያስችለናል” ብለዋል፡፡
ምንም እንኳን በሩሲያ የተወሰዱ የተለያዩ አካባቢዎችን እስካሁን መልሶ መያዝ ባይቻልም የዩክሬን ሁለተኛዋ ግዙፍ ከተማ የሆነችውን ካርኪቭ ለመቆጣጠር ተቃርቦ የነበረውን ጦር እንቅስቃሴ ማስተጓጎል ችለናል ነው ያሉት አዛዡ ፡፡
በካርኪቭ ክልል 3 አካባቢዎችን የተቆጣጠረችው ሞስኮ የዘመቻ ማስተባበርያ ቢሮዎቿን የሎጂስቲክ እንዲሁም የጦር መሳርያ መካዘኖቿን ወደ ክሪሚያ እና በአቅራቢያ በሚገኙ አካባቢዎች ላይ አስፍራለች፡፡
ዩክሬን አሁን ባገፕችው ፈቃድ ታድያ እነዚህን ስፍራዎች ኢላማ አድርጋ ለማጥቃት ቅድመ ዝግጅት እደረገች መሆኑ ተሰምቷል፡፡
እንደ ዩክሬን መከላከያ ሚንስቴር መረጃ ከሆነ በቤልጎሮድ የሚገኝው የክፍለጦር እዝ ፣ በቮሮነዝ ያለው የጥይት መካዘን፣ በክራስናዶር ያለው የድሮን ማዘዣ ጣብያ እንዲሁም የባህር ሀይሉ ለማጥቃት የእቀባው መነሳት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡
የብሔራዊ ደህንነት አጥኝው ኦሌክሲ ሜለነይክ እንደሚሉት ከአሜሪካ እና ከምእራባውን ዩክሬን በቀጣይ የምታገኛቸው የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎች፣ ድሮኖች እና ሮኬቶች የሩስያን ኢላማዎች በቀላሉ ለማጥቃት እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የታጠቁ ናቸው፡፡
ከዚህ ቀደም ዩክሬን በሩሲያ ድንበር ውስጥ ጥቃት ለመፈጸም የምትጠቀምባቸው ድሮኖች በቀላሉ በሞስኮ ራዳር ውስጥ የሚገቡ እና ጥቃት ከመፈጸማቸው በፊት ተመተው የሚወድቁ ነበሩ ብለዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በዩክሬን ድንበር እና ድንበር አቅራብያ የሚገኙ የሮኬት ማስወንጨፍያ ተሸከርካሪዎች እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች እንዲያፈገፍጉ የእቀባው መነሳት የሚኖረው ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡
እናም ጦርነቱ በጥቂቱም ቢሆን ለመመጣን እድል ኖረዋል ተብሏል፡፡
በዘንድሮው የኔቶ ጉባኤ አሜሪካ ለዩክሬን ካነሳችው እቀባ ባለፈ በጀርመን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳይሎችን ለማሰማራት እቅድ ይዛለች፡፡
ድርጊቱ ጠብ አጫሪነት ነው ያለው ክሪሚሊን በበኩሉ አውሮፓ በሙሉ በሚሳኤሎቻችን ኢላማ ውስጥ ነው የሚገኝው ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡