ትራምፕ ስለአንድነት አስፈላጊነት በተናገሩበት ቃለ ምልልስ ምን አሉ?
የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ቅዳሜ በፔንስልቬንያ የግድያ ሙከራ ከተደረገባቸው በኋላ በሰጡት ቃለ ምልልስ"ሟች ነበርኩ" ሲሉ ተናገረዋል
በትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ፈጽሟል ስለተባለው እና በቦታው በኤፍቢአይ ስለተገደለው የ20 አመቱ ቶማስ ማቲው ክሩክስ ብዙ መረጃ አልተገኘም
ትራምፕ የግድያ ሙከራ ከተደረገባቸው በኋላ በሰጡት ቃለ ምልልስ ምን አሉ?
የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ቅዳሜ በፔንስልቬንያ የግድያ ሙከራ ከተደረገባቸው በኋላ ስለአንድነት አስፈላጊነት በሰጡት ቃለ ምልልስ "ሟች ነበርኩ" ሲሉ ተናገረዋል።
ከግድያ ሙከራው በኋላ በሰጡት በአንደኛው ቃለ መጠይቅ፣ "በእድል ወይም በፈጣሪ" መትረፋቸውን ለወግ አጥባቂ የአሜሪካ ሚዲያዎች መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል
"በጣም የሚገርመው ነገር ጭንቅላቴን መመለሴ ብቻ ሳይሆን፣ በትክክለኛው ሰአት እና መጠን መመለሴ ነው"ያሉት ትራምፕ ጆሯቸውን ታክካ ያለፈችው ጥይት ልትገላቸው እንደመትችል ተናግረዋል።
"ሞቼ ነበር፣እዚህ አልገኝም ነበር" ብለዋል ትራምፕ።
በጥቃቱ አንድ ታዳሚ ሲገደል ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ በጽኑ ቆስለዋል። ጥቃት በማድረስ የተጠረጠረው ቶማስ ማቲው ክሩክ የተባለው ግለሰብም ተገድሏል።
ትራምፕ ተኩስ እንደተከፈተባቸው ከተረዱ በኋላ በቦታው የነበረውን ህዝብ በዚያ ቅጽበት ምን እንደሚመስል ገልጸዋል።
"በወቅቱ(ተኩስ ሲከፈት)በቦታው ከህዝቡ ኃይል ይወጣ ነበር፤ እዚያው ቆመው ነበር። ያን ስታይ ምን እንደሚሰማህ ለመግለጽ ከባድ ነው፤ ነገርግን አለም እያየ ነው"
ትራምፕ "ታሪክ ይህን ይፈርዳል፤ ደህና እንደሆንን እንዲያውቁ መናገር ያለብን ይመስለኛል" ብለዋል።
በዊስኮንሲን ሚልዋኩይ በሚካሄደው የሪፐብሊካን ናሽናል ኮንቬንሽን(አርኤንሲ) ለመሳተፍ ወደ አውሮፕላን ለመግባት እየተዘጋጁ በነበረበት ሰአት አሁን "ሀገሪቱን አንድ የማድረግ እድል" እንዳላቸው ተናግረዋል።
በስብሰባው ትራምፕ የሪፐብሊካን እጩ ፕሬዝደንትነታቸው እንደሚረጋገጥ ይጠበቃል።
ትራምፕ ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ በፊት አዘጋጅተውት የነበረው እና በዋናነት የባይደንን ፖሊሲ ይተች የነበረው ንግግር ፍጹም የተለያየ መሆኑን ተናግረዋል።
"የቅዳሜው ጥቃት ባይፈጸም ኖር፣ በጣም የተለየ ንግግር ይሆን ነበር።"
"እውነት ለመናገር አሁን ያለው ንግግር ፉጹም የተለየ ነው። ይህ ሀገሪቱን ወደ አንድ የማምጣት እድል አለው።"
ቀደም ሲል ትራምፕ ወደ ዊንስኮንሲን የሚያደርጉትን ጉብኝት በሁለት ቀናት እንደሚያራዝሙት ትሩዝ በተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያቸው ገልጸው ነበር። ነገረግን ቆየት ብለው ፕሮግራሙ በተያዘለት ጊዜ እንደሚከናውን የገለጹት ትራምፕ "ተኳሹ ወይም ሊገድለኝ የነበረው እቅድ እንዲያሰርዘኝ አልፈቅድም" ሲሉ ተናግረዋል።
ትራምፕ የግድያ ሙከራው ተጽዕኖ እንዳደረሰባቸው ተናግረዋል።
በትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ፈጽሟል ስለተባለው እና በቦታው በፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ስለተገደለው የ20 አመቱ ቶማስ ማቲው ክሩክስ ብዙ መረጃ አልተገኘም።
ኤፍቢአይ ምርመራው ክሩክስ ብቸኛ እንደሆነ ቢያሳየውም፣ ሌላ ተባባሪ ስለመኖሩ ወይም ስላለመኖሩ ለማወቅ ምርመራውን እንደሚቀጥል ገልጿል።የግድያ ሙከራው አለምአቀፍ ውግዘትን አስተናግዷል።
በአሜሪካ ዲሞክራሲ "ግድያ ቦታ የለውም" ሲሉ ሙከራውን ያወገዙት የአሁኑ ፕሬዝደንት ባይደን አሜሪካውያን እንዲረጋጉ እና አንድ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።