የፈረንጆቹ 2022 ከገባ ወዲህ ሰሜን ኮሪያ ለ9ኛ ጊዜ ሚሳየል አስወነጨፈች
ሀገሪቱ ሚሳኤሉን ያስወነጨፈችው ወደ ኮሪያ የባህር ወሽመጥ አቅጣጫ ነው ተብሏል
ደቡብ ኮሪያና እና ጃፓን የሰሜን ኮሪያን ተደጋጋሚ ድርጊት አውግዘዋል
የፈረንቹ 2022 ከገባ ወዲህ ሰሜን ኮሪያ ለዘጠነኛ ጊዜ ሚሳየል ማስቀንጨፋ ተገልጿል፡፡
በተደጋጋሚ ሚሳየሎችን በማስወንጨፍ የተለያዩ ማዕቀቦች የተጣሉባት ሰሜን ኮሪያ ለዘጠነኛ ጊዜ ሚሳኤል ማስወንጨፏ ተገልጿል፡፡
የፈረንጆቹ 2022 ከገባ በኋላ ለዘጠነኛ ጊዜ የሚሳየል ሙከራ ያደረገችው ሰሜን ኮሪያ ስለ ድርጊቷ እስካሁን በይፋ ያለችው ነገር የለም፡፡
የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የደቡብ ኮሪያ ፕሬዘዳንት ጽህፈት ቤቶች በጉዳዩ ዙሪያ ባወጡት መግለጫ ሰሜን ኮሪያ ባሊስቲክ ሚሳየል ማስወንጨፏን ገልጸዋል፡፡
ገና ሶስተኛ ወሩ ላይ በሚገኘው የፈረንጆቹ 2022 ዓመት ዘጠኝ ጊዜ ሚሳየል ማስወንጨፏን የሚገልጹት እነዚህ ጎረቤት ሀገራት ከአንድ ሳምንት በፊትም የሳተላይት ሚሳኤል ወደ ባህር ክልላቸው መተኮሱን ኮንነዋል፡፡
ሰሜን ኮሪያ የአሁኑን ሚሳየል ያስወነጨፈችው ከፒዮንጋንግ አውሮፕላን ጣቢያ አቅራቢያ ሳይሆን እንዳልቀረ የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ አመራሮችን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ሚሳየልን ያስወነጨፈችው የዓለም ትኩረት ሁሉ በዩክሬን ጦርነት ሆኖ ሳለ ነው የምትለው ጃፓን በበኩሏ ይህ ተቀባይነት የለውም ብላለች፡፡
አሁን ላይ ሰሜን ኮሪያ እየጠኮሰች ያለው ሚሳየል እስከ 300 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ መጓዝ የሚችል መሆኑንም ጃፓን ገልጻለች፡፡
በሚቀጥለው ወር ፕሬዘዳንታዊ ምረጫን ለማድረግ በዝግጅት ላይ ያለችው ደቡብ ኮሪያ ጎረቤቷ ሰሜን ኮሪያ በሚቀጥለው ወር ላይ ተጨማሪ ሚሳየሎችን ልታስወነጭፍ የሚል ስጋት አይሏል፡፡
አሜሪካ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለመነጋገር ፍላጎቷን ብትገልጽም ሰሜን ኮሪያ ግን ከድርድር በፊት የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላት ጠይቃለች፡፡