የሰሜን ኮሪያ የመረጃ ጠላፊዎ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው የዲጂታል ገንዘብ መዝረፋቸው
የፒዮንግ ያንግ የመረጃ ጠላፊዎ ሌሎች ኢንተርኔት ላይ ያሉ ንብረቶችን መመንተፋቸውም ተነግሯል
ሰሜን ኮሪያ የውጭ ምንዛሪ ምንጯን ለማስፋት ወደ ዲጂታል ገንዘብ ጠለፋና ሌሎች የሳይበር ተግባራት ተሰማርታለች
የሰሜን ኮሪያ የመረጃ ጠላፊዎች እስካሁን 1.5 ትሪሊየን ዎን (1.2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር) የዲጂታል ገንዘብ (ክሪፕቶ ከረንሲ) መዝረፋቸው ተገለፀ።
የደቡብ ኮሪያ የስለላ ተቋም ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የሰሜን ኮሪያ የመረጃ ጠላፊዎች ይህንን ገንዘብ የዘረፉት ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ ነው።
በሰሜን ኮሪያ መንግስት በሚደገፈው በዚህ የኦን ላይን ገንዘብ ጠለፋ በመገባደድ ላይ ባለው የፈርንጆቹ 2022 ብቻ ከ800 ቢሊየን ዎን (626 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር) ዋጋ ያለው የዲጂታል ገንዘብ ወደ ሀገሪቱ መወሰዱን የደቡብ ኮሪያው የስለላ ተቋም አስታውቋል።
- የሰሜን ኮሪያ በይነ መረብ ጠላፊዎች በ2021 ዓመት 400 ሚሊየን ዶላር መዝረፋቸው ተገለጸ
- የሰሜን ኮሪያ መረጃ ጠላፊዎች ለኑክሌር መሳሪያ የሚውል ከ 300 ሚሊዮን ዶላር በላይ መስረቃቸው ተገለጸ
ከተዘረፈው የዲጂታል የመገበያያ ገንዘብ (ክሪፕቶ ከረንሲ) ውስጥ 100 ቢሊየን ዎን (78 ሚሊየን ዶላር) ከደቡብ ኮሪያ የተዘረፈ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።
ከኒውክሌር የጦር መሳሪያ ጋር በተገናኘ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በአሜሪካ እና በሌሎች ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ማዕቀብ የተጣለባት ሰሜን ኮሪያ የውጭ ምንዛሪ ምንጯን ለማስፋት ወደ ክሪፕቶ ጠለፋና ሌሎች የሳይበር ተግባራት ከተሰማራች ዋል አደር ብላለች።
የሰሜን ኮሪያ የበይነ መረብ ጠላፊዎች ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2021 ዓመት 400 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው የዲጂታል ገንዘብ መዝረፋቸው ይታወሳል።
ጠላፊዎቹ ከ2019 መጨረሻ እስከ 2020 ድረስም ለሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ግንባታ የሚውል ከተለያዩ ተቋማት 316.4 ሚሊዮን ዶላር መመዝበራቸው ተጠቁሟል።