ሞስኮ በሩሲያ ፌዴሬሽን ግዛት ላይ ለደረሰው የኒውክሌር ጥቃት ምላሽ እሰጣለሁ ስትለም ዝታለች
ሩሲያ በ2023 ስትራቴጂካዊ የኒውክሌር ሃይሎችን እገነባለሁ አለች።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ በ2023 ሩሲያ ስትራተጂካዊ የኒውክሌር ኃይሎች ለመገንባት ልዩ ትኩረት እንደምትሰጥ አስታውቀዋል
ሚኒስትሩ " በተመደበው የበጀት ፈንዶች ውስጥ አዲስ የመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ሚዛን መጠበቅ የግድ ነዉ" ብለዋል።
“የጦር መሣሪያ ከመሳሪያ አቅርቦት ጋር በአንድ ጊዜ መንቀሳቀስ አለበት ያሉት ሾይጉ አዲሱ የሚሳኤል መሠረተ ልማት ቀድሞውኑ በሩሲያ ስትራቴጂካዊ ሚሳኤል ኃይሎች ክፍሎች እየተገነባ መሆኑም ተናግረዋል።
''አምስት የስትራቴጂክ ሚሳኤል ኃይሎች አዳዲስ የሚሳኤል ስርዓቶችን ለመዘርጋት የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን በመገንባት ላይ ይገኛሉ'' ብለዋል የመከላከያ ሚኒስትሩ።
በተጨማሪም በሩሲያ ክራስኖያርስክ ክልል ውስጥ ለኤሮስፔስ ኃይሎች ባለብዙ ዓይነት የሙከራ ቦታ እየተገነባ ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
በዚህም በጥቅምት ወር የሩሲያ ስትራቴጂካዊ የኒውክሌር ሃይሎች በሩሲያ ፌዴሬሽን ግዛት ላይ ለደረሰው የኒውክሌር ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ የኒውክሌር ጥቃትን ለማድረስ ልምምድ ማድረጋቸውም አክለዋል።
ከፕለስትስክ ኮስሞድሮም ግዛት የተወነጨፈው ያሪስ አህጉራዊ ባላስቲክ ሚሳኤል የልምምዱ አካል መሆኑንም ጠቁመዋል።