ልዩልዩ
ኖርዎይ ወደ ሩሲያ ይሄዳሉ በሚል ስጋት በርካታ አጋዘኖችን አረደች
ይህን ችግር ለመፍታት ኖርዋይ በአርክቲክ በኩል ከሩሲያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር ተደራራቢ አጥር እየገነባች ነው
ሀገሪቱ ይህን ያደረገችው አጋዘኖቹ በሩሲያ ሙርማንስክ ግዛት የሚገኝን ጥብቅ ቦታ ስለሚግጡ እና የአካባቢው ባለስልጣናት አጋዘኖቹ ላቋረጡበት ከፍተኛ ታሪፍ ስለሚጠይቁ ነው
ኖርዎይ ወደ ሩሲያ ይሄዳሉ በሚል ስጋት ምክንያት በርካታ አጋዘኖችን እንዲታረዱ አድርጋለች።
ኖርዎይ ከዚህ በፊት ግጦሽ ፍለጋ ወደ ሩሲያ የሚሄዱ እና ተመልሰው ይመጡ ከነበሩት መካከል 40 የሚሆኑትን አጋዘኖች መርጣ እንዲታረዱ ማድረጓን አርቲ ዘግቧል።
ሀገሪቱ ይህን ያደረገችው አጋዘኖቹ በሩሲያ ሙርማንስክ ግዛት የሚገኝን ጥብቅ ቦታ ስለሚግጡ እና የአካባቢው ባለስልጣናት አጋዘኖቹ ላቋረጡበት ከፍተኛ ታሪፍ ስለሚጠይቁ ነው።
ይህን ችግር ለመፍታት ኖርዋይ በአርክቲክ በኩል ከሩሲያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር ተደራራቢ አጥር እየገነባች ነው።
አጥሩ አጋዘኖቹ እንዳይሄዱ ይከላከላል የሚል እምነት ተጥሎበታል።