ሰሜን ኮሪያ ዜጎቿ ለ11 ቀናት እንዳይስቁ ከለከለች
አልኮል መጠጣትን ጨምሮ ለ11 ቀናት ምንም ዐይነት የደስታ ምልክትን ማሳየት እንደማይቻልም ተገልጿል
ፒዮንግያንግ ያንግ ይህን ያደረገችው የሃገሪቱ መሪ አባት 10ኛ የሙት ዓመትን በማስመልከት ነው
የቀድሞውን የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኢልን 10ኛ የሙት ዓመት በማስመልከት በሀገሪቱ ለ11 ቀናት መሳቅ ተከለከለ፡፡
ኪም ጆንግ ኢል ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በአውሮፓውያኑ 2011 ሲሆን ዘንድሮ 10 ዓመት ሞልቷቸዋል፡፡
የቀድሞውን መሪ 10 ኛ የሙት ዓመት አስመልክቶም በሀገሪቱ መሳቅና መጠጥ መጠጣት መከልከሉን ዴይሊ ሜል ዘግቧል፡፡
ሰሜን ኮሪያውያን ቀደም ሲል የኪም ጆንግ ኢልን ሞቶ ለተከታታይ አስር ቀናት አስበው ይውሉ የነበሩ ቢሆንም፤ ዘንድሮ ግን ኢል ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ 10 ዓመት መሞላቱን ተከትሎ ለ 11 ቀናት ያከብራሉ ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ ባለስልጣናት በሙት ዓመቱ ምክንያት ህዝቡ ምንም አይነት የደስታ ስሜት እንዳያሳይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ለጠ/ሚ ዐቢይ የደስታ መግለጫ ላከች
ዛሬ አርብ ከደቂቃዎች በፊት በፒዮንግያንግ የነበረው የቢዝነስና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ለ5 ያል ደቂቃዎች ቆሞ የኢል 10ኛ ሙት ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት መካሄዱንም የሃገሪቱ ማዕከላዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል፡፡
ከፈረንጆቹ 1994 እስከ 2011 ሰሜን ኮሪያን ከመሩት ከኪም ጆንግ ኢል ህልፈት በኋላ ሶስተኛ ልጃቸው ኪም ጆንግ ኡን በእግራቸው ተተክቶ ሃገሪቱን እየመራ ነው፡፡
በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ የምትገኘው ሲኑይጁ ከተማ ነዋሪ የሆነ ሰሜን ኮሪያዊ ራዲዮ ፍሪ እስያ ለተባለ ሚዲያ በሰጠው አስተያየት፤ ለቀጣዮቹ 11 ቀናት መጠጥ እንደማይጠጣና እንደማይስቅ ተናግሯል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ሰሜን ኮሪያውያን ወደ ግሮሰሪ መሄድ እንደማይችሉ የተነገራቸውም ሲሆን በመታሰቢያ የዚህ የሀዘን ቀናቱ ውስጥ ቤተሰቡ የሞተበት ሰው ጮክ ብሎ ማልቀስ እንደማይችልም ሰሜን ኮሪያ አስጠንቅቃለች፡፡
ሰሜን ኮሪያውያን በኪም ጆንግ ኡን ውፍረት መቀነስ ተጨንቀው እያለቀሱ መሆኑ ተሰምቷል
የልደት በዓላቸው በ11 ዱ የሀዘን ቀናት ውስጥ የሆነባቸው ግለሰቦች ይህንን ማድረግ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋልም ነው የተባለው፡፡
በ 69 ዓመታቸው በፈረንጆቹ ታህሳስ 17 ቀን 2011 በልብ ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የሰሜን ኮሪያ መሪ ሀገራቸውን ለ 17 ዓመታት መምራታቸው ይታወሳል፡፡
ምዕራባውያን ኪም ጆንግ ኢልን እና ሃገሪቱን በመምራት ላይ የሚገኙትን ልጃቸውን ኪም ጆንግ ኡንን በአምባገነንነት ደጋግመው ሲከሱ ይደመጣሉ፡፡