ዩክሬን ጦር የነፍስ አድን ሰራተኞችን ስራ የበለጠ አደገኛ እያደረገው ነው ተብሏል
ሞስኮ የነፍስ አድን ሰራተኞቿ በዩክሬን እየተደበደቡባት መሆኑን ገለጸች፡፡
በዩክሬን ኬርሰን ክልል የሚገኘው ግዙፉ የካኮቭካ ግድብ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ጉዳት ደርሶበታል።
ክሬምሊን ጉዳቱን ተከትሎ በጎርፍ ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ ሲሰጡ የነበሩ የሩሲያ የነፍስ አድን ሰራተኞች ላይ ድብደባ አድርጋለች በማለት ዩክሬንን ከሷል።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በአካባቢው የሚገኙ የሩስያ የነፍስ አድን ሰራተኞች ጠንክረው እየሰሩ ቢሆንም የዩክሬን ጦር ስራቸውን የበለጠ አደገኛ እያደረገው ነው ብለዋል።
ዩክሬን የራሷን ድሮን በማእከላዊ ኪቭ መትታ ጣለች
ፒስኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሰራተኞቹ ከዩክሬን በሚሰነዘረው ቀጣይነት ባለው ጥቃት ውስጥ ሆነው እንዲሰሩ ተገደዋል።
የዩክሬን ባለስልጣናት በበኩላቸው በኪየቭ በተያዘው የዲኒፕሮ ወንዝ ዳርቻ ላይ የሩስያ ኃይሎች የነፍስ አድን ሰራተኞችን ደበደቡ ሲሉ ከሰዋል።
ሞስኮ ምስራቃዊ የወንዙን ዳርቻ በቁጥጥሯ ስር መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ማክሰኞ የደረሰው የካኮቭካ ግድብ ጉዳት በዲኒፕሮ ወንዝ የታችኛው ክፍል ላይ ከፍተኛ ጎርፍ አስከትሏል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል የተባለ ሲሆን፤ በወንዙ ግራና ቀኝ ያሉ መንደሮችም በውሃ ተጥለቅልቀዋል።
ፔስኮቭ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአካባቢው ያለውን ሁኔታ እየተከታተሉ ነበር ብለዋል። ነገር ግን ፑቲን በአሁኑ ጊዜ የአደጋውን አካባቢ የመጎብኘት እቅድ እንደሌላቸው ጠቁመዋል።