የዩክሬን ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ የጠላት ድሮን ተመታ ቢሉም፤ የሀገሪቱ አየር ኃይል ግን የተመታው ድሮን የሳራችን ነው ብሏል
የዩክሬን አየር ኃይል የራሱን ድሮን በኪቭ ከተማ በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቤተ መንግስት አቅራቢያ መትቶ መጣሉ ተነግሯል።
የሀገሪቱ አየር ኃይል ድሮኑን ትናንተ እኩለ ሌሊት ላይ መትቶ መጣሉን ያስታወቀ ሲሆን፤ ድሮኑን መትቶ ለመጣል በተደረገ ተኩስ በከተማዋ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምጽ ይሰማ እንደነበረ ቢቢሲ ዘግቧል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አንድሪ ዬርማክ፤ “ተመትቶ የወደቀው የጠላት ድሮን ነው” ብለው ነበረ።
የዩክሬን አየር ኃይል ቆየት ብሎ ባወጣው መግለጫ ተመትቶ የወደቀው ድሮን የሀገሪቱ መሆኑን እና ከቁጥጥራቸው ውጭ በመሆኑ ሊደርስ የሚችል ጉዳትን ለመቀነስ እርምጃው እንደተወሰደ አስታውቋል።
አየር ኃይሉ በመግለጫው ባይካር TB2 UAV ድሮኑ በተቀመጠለት መርሃ ግብር መሰረት ምሽት 4 ሰዓት ላይ በረራውን እያደረገ ከቁጥጥር ውጭ መሆኑንም አስታውቋል።
ድሮኑን መትቶ የመጣል ውሳኔ ላይ የተደረሰው ድሮኑ በከተማ ውስጥ እየበረረ ከመሆኑ ጋር የተነሳ ሊያደርሰው የሚችለውን ጉዳት መገመት አደጋች ስለሆነ ነውም ብሏል አየር ኃይሉ።
ተመትቶ ከወደቀው ድሮን ጋር በተያያዘ በቨሰው ላይ የደረሰ ሞትም ይሁን የመቁሰል አደጋ እንደለሌ ማረጋገጡንም ነው በመግለጫው አስታውቋል።
የዩክሬን አየር ኃይል አክሎም “ክስተቱ በጣም ያሳዝናል፣ ግን ይህ ቴክኖሎጂ ነው እና እንደዚህ አይነት ጉዳዮች ይከሰታሉ” ያለ ሲሆን፤ ያጋጠመው የቴከኒክ ችግር ሊሆን ይችላል፤ ምክንያ ገና እየተጣራ ነውም ብሏል።