ሩሲያ ከሰሞኑ ወደ ዩክሬን እየተኮሰችው ያለው ኪንዛል ሚሳኤል ምን አይነት ነው ?
በአሜሪካ ለዩክሬን የተገነባው ጸረ ሚሳኤል ማዕከል በኪንዛል ሚሳኤል መውደሙ ተገልጿል
ኪንዛል ሀይፐር ሶኒክ ሚሳኤል በሩሲያዊያን "ሰንጢው" በሚል ይጠራል
ሩሲያ ከሰሞኑ ወደ ዩክሬን እየተኮሰችው ያለው ኪንዛል ምን አይነት ነው?
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 15ኛ ወሩ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ መልኩን ቀይሮ እንደ አዲስ ውጊያው ቀጥሏል፡፡
- የዓለምን የኃይል ሚዛን ይለውጣል ስለሚባለው የሩሲያ "ሳርማት" ሚሳኤል ምን ያውቃሉ?
- ሰሜን ኮሪያ በጠላት ላይ "ከፍተኛ ቀውስ" ያስከትላል ያለችውን ሚሳይል መሞከሯን አስታወቀች
ዩክሬን ከወዳጅ ሀገራት ያሰባሰበቻቸው ዘመናዊ የአየር እና የምድር ላይ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በማቀናጀት በሩሲያ ላይ አዲስ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ጀምራለች፡፡
ሩሲያም የዩክሬንን መልሶ ማጥቃት ዘመቻዎችን በመመከት ላይ መሆኗን የገለጸች ሲሆን ጥቃቱ በዋነኛነት በዩክሬን የጦር መሳሪያ መሰረተ ልማቶች ላይ አነጣጥራለች፡፡
በዚህም ጥቃት ዩክሬን ከተለያዩ ወዳጅ ሀገራት ያሰባሰበቻቸው የጦር መሳሪያ እና ማከማቻዎችን ማውደሟን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ሩሲያ በዩክሬን መዲና በአሜሪካ የተገነባው የጸረ ሚሳኤል ጥቃት ማክሸፊያ ማዕከል ኪንዛል በተሰኘው የሩሲያ ሀይፐር ሶኒክ ሚሳኤል ጥቃት ደርሶበታል፡፡
ባለፉት ወራት ጥቅም ላይ እንዳልዋለ የተገለጸው ይህ ዘመናዊ ሚሳኤል በሰዓት ከ12 ሺህ በላይ ኪሎ ሜትር ርቀት መጓዝ ይችላል ተብሏል፡፡
480 ኪሎ ግራም ይመዝናል የተባለው ኪንዛል ሚሳኤል የቀጣዩ ትውልድ ይታጠቀዋል ተብሎ ከሚጠበቁ ስድስት ሚሳኤሎች ውስጥ አንዱ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ሩሲያ በፈረንጆቹ 2018 ላይ እንደሰራችው ይፋ ያደረገችው ይህ ሚሳኤል በ2021 ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶሪያ እንደተሞከረ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናግረዋል፡፡
ኪንዛል ሀይፐር ሶኒክ ሚሳኤል በአሁኑ ሰዓትም ወደ ዩክሬን እየተተኮሰ ሲሆን ሩሲያ ውጤታማ መሆኑን ስትናገር ዩክሬን በበኩሏ ስድስት ኪንዛል ሚሳኤል እንደተተኮሰባት እና ሁሉንም መትታ መጣሏን ገልጻለች፡፡