የኒዩክሌር ጦርነት የአለማችን ቀጣዩ ስጋት ነው
አሜሪካ ከ78 አመት በፊት ሀምሌ 16 1945 የፕሉቱኒየም ቦምብ በኒው ሜክሲኮ ሞክራለች።
18 ነጥብ 6 ኪሎቶን ሃይል የለቀቀው ይህ የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ የአቶሚክ ዘመን ጅማሮ ተደርጎ ይወሰዳል።
ከዚህ ሙከራ በኋላ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አሜሪካ በጃፓን ሄሮሺማ እና ናጋሳኪ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎችን የገደሉ የአቶሚክ ቦምቦችን መጣሏ ይታወሳል።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ከ100 ሺህ በላይ ሰዎችም ከአመታት በኋላ ለህልፈት መዳረጋቸውን የመንግስታቱ ድርጅት መረጃ ያሳያል።
የኒዩክሌር የጦር መሳሪያ ሙከራ የሚያደርሰውን ጉዳት በተመለከተ ግንዛቤ ለማስጨበጥም ድርጅቱ በየአመቱ ነሃሴ 29 የኒዩክሌር መሳሪያ እንዳይሞከር የሚወተወትበት ቀን እንዲሆን ወስኗል።
ይሁን እንጂ ሩሲያን ጨምሮ ስምንት ሀገራት እስከ 2017 ድረስ ከ2 ሺህ ጊዜ በላይ የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ ማድረጋቸውን የመሳሪያ ቁጥጥር ተቋም (አርምስ ኮንትርል አሶሼሽን) መረጃ ያሳያል።
በሰው ልጆች ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሰውን የኒዩክሌር መሳሪያ እስካሁን እነማን ሞክረውታል? በቀጣዩ ስዕላዊ መረጃ ይመልከቱ፦