ኒውክሌር የታጠቁ ሀገራት በ2021 ብቻ 82.4 ቢሊየን ዶላር ለጦር መሳሪያ ወጪ አድርገዋል ተባለ
ሀጋረቱ የአቶሚክ መሳሪያቸውን ለማሻሻልነው በቢሊየን ዶለር የሚቆጠር ዶላር ያፈሰሱት
በዓለም ላይ 9 ሀገራት የኒውክሌር የጦር መሳሪያን ታጥቀዋል
የኒውክሌር የጦር መሳሪያን የታጠቁ 9 ሀገራት በፈረንጆቹ 2021 ብቻ የአውቶሚካ መሳሪያቸውን ለማሻሻል 82.4 ቢሊየን ዶላር ወጪ ማድረጋቸው ተገለፀ።
ሀገራቱ በፈረንጆቹ 2021 ወጪ ያደረጉት ገንዘብ ከባለፈው 2020 ጋር ሲነጻተር በ8 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱም አይካን የተባለ በኒውክሌር የጦር መሳሪያ ላይ የሚሰራ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት አመላቷል።
ከፍተኛ ወቺ ካወጡ ሀገራት ውስጥ አሜሪካ ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዝ ሲሆን፤ በሪፖርቱ ላይ ከተመላከተው አጠቃላይ ወጪ ግማሽ ያክሉ የአሜሪካ መሆኑ ተነግሯል።
ቻይና እና ሩሲያ ተከታዩን ደረጃ የያዙ ሲሆን፤ ብሪታኒያ እና ፈረንሳይም በኒውክሌር ጦር መሳሪያ ላይ ከፍተኛ ወጪ ያወጡ ሀገራት ተብለው ተዘርዝረዋል።
ኢኮኖሚዋ በተባበሩት መንግስታት ማዕቀብ በእጅጉ የተጎዳው ሰሜን ኮሪያም በፈረንጆቹ 2021 ብቻ 642 ሚሊየን ዶላር ደገማ በኒውክሌር የጦር መሳሪያ ላይ ወጪ ማድረጓን በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ቡድኑ በሪፖርቱ “አብዛኞቹ የአለም ሀገራት የአለም አቀፍ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እገዳን ይደግፋሉ” ሆኖም ግን የኑክሌር የታጠቁ ሀገራት በ2021 በህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች ላይ በርካታ ገንዘብ አውጥተዋል” ብሏል።
የስቶክሆልም አለም አቀፍ የሰላም ጥናትና ምርምር ባሳለፍነው ሰኞ እለት ባወጣው መግለጫው “ዘጠኙም የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ታጠቁ ሀገራት መሳሪያዎቻቸውን እያሳደጉ ወይም እያሻሻሉ መሆናቸውን እና የጦር መሳሪያዎቹ ጥቅም ላይ የመዋል ዕድል ከቀዝቃዛው ጦርነት ጊዜ በኋላ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ከፍ ብሏል” ሲል አስጠንቀወቋል።