ከልክ ላለፈ ውፍረት ተጠቂዎች የተሰራው አዲስ መድሃኒት የባለሀብቶችን ትኩረት ስቧል
መድሃኒቱ በፍጥነት እየጨመረ ለመጣው ከልክ ያለፈ ውፍረት መፍትሔ እንደሚሆን ታምኖበታል
ከ10 ዓመት በኋላ የዓለማችን ግማሽ ያህል ህዝብ ከልክ ያለፈ ውፍረት ሰለባ ሊሆን ይችላል በሚል ተሰግቷል
ከልክ ላለፈ ውፍረት ተጠቂዎች የተሰራው አዲስ መድሃኒት የባለሀብቶችን ትኩረት ስቧል፡፡
ከልክ ያለፈ ውፍረት ተጠቂ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ታስቦ የተሰራው መድሃኒት የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎችን ትኩረት እንደሳበ ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት ባሳለፍነው ዓመት ባወጣው ሪፖርት ከልክ ያለፈ ውፍረት እየጨመረ መሆኑን ገልጾ በፈረንጆቹ 2035 ላይ ግማሽ ያህሉ የዓለማችን ህዝብ ከልክ በላይ ለሆነ ውፍረት ይጋለጣል ብሏል፡፡
ለደም ግፊት፣ ስኳር እና ሌሎች ጽኑ ህመሞች ምክንያት የሆነው ከልክ ያለፈ ውፍረት አመጋገብን በማስተካከል እና የአካል ብቃት እንቅስቃ በማድረግ መከላከል ይቻላልም ተብሏል፡፡
- ውፍረት ለመቀነስ የሚጥሩ ሰዎች እስከ 5 ዓመት ለልብና ስኳር ህመም የመጋለጥ እድላቸውን ይቀንሳሉ - ጥናት
- በ2035 ግማሹ የዓለም ህዝብ ከልክ ላለፈ ውፍረት ይጋለጣል ተባለ
ተመራማሪዎች ከልክ ያለፈ ውፍረትን ለመከላከል ክብደት እንዲቀንስ የሚያደርግ መድሃኒት መስራታቸውን የገለጸው ይህ ዘገባ ከልክ ባለፈ ውፍረት የተጠቁ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ የመድሃኒቱን ተፈላጊነት እንዳሳደገው ተገልጿል፡፡
የአሜሪካዎቹ ኤሊ እና ዳኒሽ መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች ከልክ በላይ ውፍረት ላለባቸው ሰዎች ተስማሚ የሆነ መድሃኒት መስራታቸውን አስታውቀዋል፡፡
መድሃኒቱ በተለይም የሚያደርሳቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች አነስተኛ መሆኑ እስካሁን የተደረጉ ሙከራዎች ያስረዳሉም ተብሏል፡፡
አዲሱ መድሃኒት ሰዎች ከወሰዱት በኋላ ለአእምሯቸው ምግብ እንደበሉ እና ሆዳቸው ሙሉ እንደሆነ የሚገልጽ መልዕክት በማድረስ ለውፍረት የመዳረግ እድልን እና የምግብ ፍላጎትን እንዲቀንሱ ያደርጋል፡፡
ይህን ተከትሎም ይህን መድሃኒት የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች ትኩረታቸውን ይህንን መድሃኒት ወደማምረት እያደረጉ እንደሆነ ተገልጿል፡፡