እረፍት ላይ የነበረ አብራሪ በድንገት የታመመን አብራሪ ተክቶ አውሮፕላኑ እንዲያርፉ አደረገ
ኤየር ካናዳ ስለታመመው ፖይለት ጉዳይ ያለው ነገር የለም
በካናዳ እረፍት ላይ የነበረ ፖይለት በድንገት የታመመውን አብራሪ በመተካት አውሮፕላኑ እንዲያፍ ማድረጉ ተገለጸ
በካናዳ በሀገር ውስጥ በረራ ወቅት እረፍት ላይ የነበረ ፖይለት በድንገት የታመመውን አብራሪ በመተካት አውሮፕላኑ እንዲያፍ ማድረጉ ተገለጸ።
የኤየር ካናዳ አየርመንገድን አውሮፕላን ሲያበሩ ከነበሩት ውስጥ አንዱ በሀገር ውስጥ በረራ ወቅት ድንገት ይታመማል። ይህን ጊዜ እረፍት ወስዶ በጊዞ ላይ የነበረው አብራሪ የታመመውን አብራሪ በመተካት አውሮፕላኑ እንዲያርፍ አድርጓል።
ኤየር ካናዳ ከቶሮንቶ ወደ ሴንት ጆን በተደረገው በረራ መጨረሻ አካባቢ የመጀመሪያው አብራሪ የህመም ስሜት እንደተሰማው ገልጿል።
አየር መንገዱ እንደገለጸው በእረፍት ላይ የነበረው የኤየር ካናዳ ፖይሌት የታመመውን የመጀመሪያውን ፖይለት በመተካት፣ እንደተለመደው ሁለት ፖይለቶች በሰላም አውሮፕላኑን አሳርፈውታል።
ኤየር ካናዳ ስለታመመው ፖይለት ጉዳይ ያለው ነገር የለም።
ኤየር ካናዳ 140 መንገደኞችን መጫን የሚችል ኤ-220 የተሰኙ ባለሁለት ሞተር የኤርባስ አውሮኘላኖችን የሚጠቀም ድርጅት ነው።