የሩሲያ ወታደራዊ አውሮኘላን በሳይቤሪያ ግዛት ተከሰከሰ
የመከስከስ አደጋው በስድስት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው
በመከስከስ አደጋው የሁለት አብራሪዎች ህይወት ማለፉን ባለስልጣናት ተናግረዋል
የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላን በሳይቤሪያ ግዛት ባጋጠማት የመከስከስ አደጋ የሁለቱ አብራሪዎች ህይወት ማለፉን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
አውሮፕላኗ በሳይቤሪያ ግዛት በምትገኘው ኢርኩስቲክ ከተማ ተከስክሳለች፤አብራሪዎቹም ህይወታቸው ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል።
የእርኩስቲክ አስተዳዳሪ ኢጎር በቴሌግራም ገጻቸው ኮብዜቭ አውሮኘላኗ የተጋጨችው ከባሁለት ፎቅ መኖሪያ ቤት ጋር ነው ብለዋል።
የመከስከስ አደጋው በስድስት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ባለፈው ሰኞ ሱ 34 ተዋጊ አውሮፕላን በደቡባዊ ከፍል በምትገኘው የይሴክ ከተማ በሚገኝ የመኖሪያ መንደር ተከስክሳ በትንሹ 15 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
በዛሬው እለት አደጋ የደረሰባት አውሮፕላን ሱ30 እንደሆነች ሮይተር ጠቅሷል።
የአደጋዎች ሚኒስቴር እንደገለጸው አደጋው የደረሰው በሙከራ በረራ ሳለ ነው ብለዋል።