የሮማው ሊቀ ጳጳስ በገልፍ የምትገኘውን ጥንታዊ ቤተክርስትያን ጎበኙ
አባ ፍራንሲስ ፤ የሃይማኖት አባቶች አንድነታቸውን በማጠናከር ለቀጣነው ሰላም የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጠይቀዋል
ባህሬን ወደ 160ሺህ የሚጠጉ ካቶሊኮች ያሏት ሲሆን አብዛኞቹ የውጭ ሀገር ሰራተኞች መሆናቸውም ይነገራል
የሮማ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በገልፍ የምትገኘውን ጥንታዊ ቤተክርስትያን በመጎብኘት የባህሬን ጉዞዋቸውን አጠናቀዋል፡፡
አባ ፍራንሲስ እንደፈረንጆቹ በ1939 የተገነባውን አንጋፋውን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን በጎበኙበት ወቅት ሙስሊም በሚበዛበት አካባቢዎች ምእመናንን ሲያገለግሉ ያገኙዋቸውን ጳጳሳት፣ ቀሳውስትና መነኮሳት አንድነታቸውን አንዲያጠናክሩ ምክራቸው ለግሰዋል፡፡
“ዓለማዊ መለያየት እንዲሁም የብሔር፣ የባህልና የስርዓት ልዩነቶች የመንፈስን አንድነት ሊጎዱ ወይም ሊያናጉ አይችሉም” ብሏቸዋል፡፡
የሃይማኖት አባቶች ለቀጣነው ሰላም የራሳቸውን ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባም ተናግረዋል ሊቀ ጳጳሱ፡፡
ባህሬን በአረብ ባሕረ ሰላጤው ትልቁ ቤተ ክርስቲያን የሆነውን ዘመናዊ ካቴድራልን ጨምሮ ሁለት የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት አሏት፡፡
በተጨማሪም ወደ 160ሺህ የሚጠጉ ካቶሊኮች ያሏት ሲሆን አብዛኞቹ የውጭ አገር ሰራተኞች መሆናቸውም ይነገራል፡፡
በሰሜን አረቢያ በአራት ሀገሮች ውስጥ በተሰራጩት በግምት 2 ሚሊዮን ካቶሊኮች መካከል ወደ 60 የሚጠጉ ቀሳውስት እንደሚሰሩ የቫቲካን ሐዋርያዊ አገልግሎት ሊቀ ጳጳስ ፖል ሂንደር ተናግረዋል።
በቤተክርስቲያኑ አገልግሎት ማብቂያ ላይ የሮማው ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ “ለተሰደራገላቸው አስደናቂ መስተንግዶ” የባህሬኑን ንጉስ ሃማድ ቢን ኢሳ አል ካሊፋን አመስግነዋል።
በባህሬን እና በባህረ ሰላጤው አካባቢ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ካቶሊኮች ሊቀ ጳጳሱ ቅዳሜ ቅዳሴ ሲያሰሙ ለመስማት ወደ ስታዲየም መግባታቸውም ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ፍራንሲስ ጉብኝት እንደፈረንጆቹ በ2019 በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያደረጉትን ታሪካዊ ጉብኝት በኋላ የተገደረገ ሲሆን፤ ከእስላማዊው ዓለም ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል የሚከተሉትን ፖሊሲ አጠናክረው ለመቀጠል ያላቸውን ፍላጎት የሚያመላክት ነው ተብሎለታል፡፡