የአዛውንቱ ቤተሰቦች እስራቱን "የሞት ፍርድ ያህል ነው" ሲሉ ገልጸውታል
በኢራቅ ጥንታዊ ቅርሶችን ይዞ የተገኘው ብሪታኒያዊ 15 ዓመት ተፈረደበት፡፡
በሙያው ጂኦሎጂስት ነው የተባለለት የ66 ዓመቱ ጂም ፊቶን ጥንታዊ ቅርሶችን ከኢራቅ በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር ነበር በሚል ነው እስራት የተፈረደበት፡፡
ጉዳዩን የተመለከተው የሃገሪቱ ፍርድ ቤት 15 ዓመታት እንዲታሰር ፈርዶበታል፡፡
ፍርዱ የጡረተኛውን ጂኦሎጂስትና ጠበቆች አስደንግጧል፡፡
ፊቶን ወንጀል ለመስራት በማሰብ ድርጊቱን እንዳልፈጸመው የገለጹት ቤተሰቦች እስራቱን "የሞት ፍርድ ያህል ነው" ሲሉ ገልጸውታል፡፡
ደንበኛው ጥፋተኛ ቢሆን እንኳ ጉዳዩ ከአንድ ዓመት በላይ ሊያሳስር የሚችል እንዳልነበረም ነው ጠበቃው የተናገረው፡፡
ከብሪታኒያ እስከ አዘርባጃን፡ ፑቲን "ተደርገውብኝ ነበር" ካሏቸው አምስት የግድያ ሙከራዎች እንዴት ተረፉ?
ፊቶን ባሳለፍነው ወርሃ መጋቢት አጋማሽ አካባቢ ነው በሻንጣው ይዟቸው በነበሩ ጥንታዊ ቅርሳ ቅርሶች ምክንያት በባግዳድ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የተያዘው፡፡
በወቅቱ አብሮት የነበረ አንድ ጀርመናዊ በአየር ማረፊያው የደህንነት አካላት መያዙንም ነው የብሪታኒያ ጋዜጦች የዘገቡት፡፡ ሆኖም ጀርመናዊው ጥፋተኛ አለመባሉን ተከትሎ ከእስር ነጻ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል፡፡