የጃፓን የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ በጥይት ተመተው ከተገደሉ አንድ ዓመት ሆናቸው
የ67 ዓመቱ ሺንዞ አቤ ከ"አንድነት ቤተክርስቲያን" ጋር በነበራቸው ግንኙነት በአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል
የሺንዞ አቤ ሞት ለመሳሪያ ጥቃት እንግዳ የሆነችውን ሀገር አናውጧል
የጃፓን የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ ባለፈው ዓመት የምርጫ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበረበት ወቅት በጥይት ተገድለዋል።
የጃፓን የረዥም ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ሞት ለመሳሪያ ጥቃት እንግዳ የሆነችውን ሀገር አናውጧል።
ጠቅላይ ሚንስትር ፉሚዮ ኪሺዳ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በቶኪዮ በሚገኘው የቡዲስት ቤተ መቅደስ መታሰቢያ ስነ ስርዓት አድርገዋል።
ስነ ስርዓቱ ካለቀ በኋላ ህዝቡ አበባ እንዲያቀርብ ተፈቅዶለታል።
ሺንዞ አቤ ለዓመታት የዘለቀውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር የታለሙ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን በመከተል የሚታወሱ ናቸው።
በተቺዎች ደግሞ እነዚህ እርምጃዎች የገቢ ክፍተትን ከፍተዋል በሚልም ይወቀሳሉ።
በፈረንጆቹ 2020 ስልጣናቸውን የለቀቁት አቤ፤ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የጃፓን ወታደሮች ወደ ባህር ማዶ እንዲዋጉ የሚያስችለውን ወታደራዊ ወጪን የሚጨምርና ጦርነት በህገ መንግስቱ እንደገና የተረጎመ የመከላከያ ፖሊሲ ደግፈዋል።
ኪሺዳ ከአቤ የኢኮኖሚ አጀንዳ ወደ ኋላ ቢያፈገፍጉም፤ ጃፓን የመከላከያ ወጪን በእጥፍ እንደምትጨምር ባለፈው ዓመት በማስታወቅ የቀድሞ መሪውን ፖሊሲዎች አስጠብቀዋል።
የ67 ዓመቱ ሺንዞ አቤ ከ"አንድነት ቤተክርስቲያን" ጋር በነበራቸው ግንኙነት ምክንያት ነበር የተገደሉት።