ከተጀመረ 1 ዓመት ያስቆጠረው የሱዳን ጦርነት፤ መፍትሄ ያልተገኘለት ቀውስ…
በሱዳን ጦርና እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የተቀሰቀሰው የሱዳን ጦርነት ትናንት አንድ ዓመት ሞልቶታል
በጦርነቱ ከ14 ሺህ በላይ ሱዳናዉያን ሞተዋል፤ 8 ሚሊየን ሱዳናውያን ተፈናቅለዋል
በፈረንጆቹ ሚያዝያ 15፣ 2023 በሱዳን ጦርና እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የተቀሰቀሰው የሱዳን ጦርነት ትናንት አንድ ዓመት ሞልቶታል።
ምክንያቱ ምንድን ነው?
በሱዳን የሲቪል የሽግግር መንግስት ለመመስረት ሲደረግ የነበረው ድርድር የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉን ወደ ብሄራዊ ጦሩ የመቀላቀያ ቀነ ገደብ ማስቀመጡ ለግጭቱ ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ ቢጠቀስም ኩርፊያ እና የስልጣን ሽኩቻው የቆየ እንደሆነ ይነገራል።
የተቆጣጠሯቸው ቦታዎች የትኞች ናቸው?
የቀይ ባህር፣ ካሳላ፣ ገዳሪፍ፣ ሴናር፣ ብሉ ናይል፣ ሰሜን እና አባይ ወንዝ እንዲሁም የነጭ አባይ፣ የሰሜን ኮርዶፋን፣ የምዕራብ ኮርዶፋን እና የደቡብ ኮርዶፋ ግዛቶችን ቆጣጥሮ ይገኛል።
ጦርነቱ ምን ጉዳት አስከተለ?
ከ14 ሺህ በላይ ሱዳናዉያን ሞተዋል፤ 8 ሚሊየን ሱዳናውያን ተፈናቅለዋል፤ 18 ሚሊየን ሰዎች ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል።
በጦርነቱ ዙሪያ የተደረጉ ስምምነቶና ውይይቶች?
ሚያዝያ 16, 2023 .. በሱዳን ጉዳይ ላይ የአረብ ሊግ አስቸኳይ ስበስባ ተደረገ፤ ሚያዝያ 25, 2023 .. አሜሪካ ሁለቱ ወገኖች የ72 ሰዓት ተኩስ አቁም ማድረጋቸውን አወጀች፤ ሐምሌ13, 2023 .. የሱዳን ጎረቤት ሀገራ ስብሰባ በካይሮ
የጦርነቱ መጨረሻ ምን ሊሆን ችላል?
- ቀውሱ በቅርቡ መጠናቀቁን የሚጠቁሙ ምልክቶች የሉም፤ ውስጣዊ አንድነት እና ክልላዊ ደህንነት ላይ አደጋዎችን ይደቅናል
በእርስዎ አስተያየት.. ሱዳን ለችግሯ በቅርቡ መፍትሄ ልታገኝ ትችላለች?