አንድ አመት ያስቆጠረው የሱዳን ጦርነት እንዳይቆም ያደረገው ምክንያት ምንድነው?
የሱዳን ጦር ባለው ሶስት ሚሊዮን ተዋጊ እና በአየር ኃይል የበላይነት ቢወስድም፣ የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በደንብ የታጠቀ 100ሺ ጦር መገንባት ችሏል
በሱዳን ከአንድ አመት በፊት ህዝብ እንዲፈናቀል እና በዳርፉር ግዛት የብሄር ግጭት እንዲቀሰቀስ ምክንያት የሆነው ጦርነት አሁንም አልቆመም
አንድ አመት ያስቆጠረው የሱዳን ጦርነት እንዳይቆም ያደረገው ምክንያት ምንድነው?
በሱዳን ከአንድ አመት በፊት ተቀስቅሶ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ እንዲፈናቀል እና በዳርፉር ግዛት የብሄር ግጭት እንዲቀሰቀስ ምክንያት የሆነው ጦርነት አሁንም አልቆመም።
የግጭቱ መነሻ
ባለፈው አመት ሚያዝያ አጋማሽ ግጭቱ ከመቀስቀሱ በፊት በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል ለወራት የቆየ ውጥረት ነበር።
የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በ2ዐ21 በትብብር የሲቪል መንግስቱን ከስልጣን ካስወገዱ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ ነበር አለመግባባት ውስጥ የገቡት።
የሁለቱ ሀይሎች አለመግባባት ገሀድ የወጣው ሀገሪቱ በሲቪል አስተዳደር እንድትመራ ለማድረግ በተጀመረው እና አለምአቀፍ ድጋፍ ባለው የሽግግር እቅድ ምክንያት ነበር።
በእቅዱ መሰረት የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ስልጣን ለሲቪል መንግስት አሳልፈው እንዲሰጡ የሚያደርግ ነው።
በዚህ እቅድ ውስጥ የተካተቱት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወደ ሱዳን ጦር የሚካተቱበት ቀነገደብ እና በመካከላቸው የሚኖረው የስልጣን ክፍፍል አጨቃጫቂ ጉዳዮች ሆነው ሊወጡ ችለዋል።
የግጭቱ ዋና ተዋናዮች እነማን ናቸው?
የግጭቱ ዋና ተሳታፊዎች የሱዳን ጦርን የሚመሩት ጀነራል አልቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃሎችን የሚመሩት ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ ናቸው።
ጦርነቱ በተጀመረ ሰሞን ሁለቱ ጀነራሎች ከህዝብ እይታ ተሰውረው ነበር።
ነገርግን ቆየት ብለው አልቡርሃን በቀይ ባህሯ የወደብ ከተማ ሆነው መግለጫ መስጠት ጀመሩ።ሁለቱ ጀነራሎች ወደ ውጭ ጉዞ በማድረግ ድጋፍ ለማሰባሰብ ጥረት አድርገዋል።
በአልበሽር የስልጣን ዘመን ከመንግስት ጦር ጋር ሆነው በዳርፉር አማጺያን ጥቃት በማድረስ ሚና የነበራቸው ሄሜቲ በማዕድን ምርት የተሰማሩ ሀብታም ናቸው።
ማን እያሸነፈ ነው?
ምንምእንኳን የሱዳን ጦር ባለው ሶስት ሚሊዮን ተዋጊ እና በአየር ኃይል የበላይነት ቢወስድም፣ የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በደንብ የታጠቀ 100ሺ ጦር መገንባት ችሏል።
ጦርነቱ በተጀመረበት የመጀመሪያዎቹ ቀናት የተበጣጠሰ አሀድ ያላቸው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወታደሮች በዋና ከተማዋ ካርቱም መሸጉ። በ2023 መጨረሻ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የዳርፉር ይዞታቸውን አጠናከሩ፣ በደቡባዊው ካርቱም የምትገኘውን እና በግብርና የምትታወቀውን አል ገዚራ ከተማም ተቆጣጠሩ።
ይሁን እንጅ በቅርቡ የካርቱም አካል ከሆኑት ሶስት ከተሞች ውስጥ የሱዳን ጦር የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን ይዞታ ማስለቀቅ ችሏል።
የዓለም ኃያላን እና በርካታ የአረብ ሀገራት በሱዳን ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ውድድር ውስጥ መግባታቸው ጦርነቱ እንዳይቆም ምክንያት ሆኗል።
የገልፍ ሀገራት በግብርና እና በወደብ ጨሞሮ በበርካታ ዘርፎች ኢንቨስት የማድረግ እቅድ ነበራቸው። ሩሲያ በቀይ ባህር ዳርቻ የባህር ኃይል ሰፈር እንዲኖራት ትፈልጋለች።
አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት ደግሞ በሀገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንዲደረግ ይፈልጋሉ።
ለሱዳን የተሰጠው የዲፕሎማሲ ትኩረት በዩክሬን እና በጋዛ ባሉት ጦርነቶች ምክንያት ቀንሷል።