የካርቱም ነዋሪዎች በምግብ እጥረት እና እየተስፋፋ በመጣው ዝርፊያ ምክንያት ከባድ ጊዜ እያሳለፉ ናቸው
በዲፕሎማሲ መፍትሄ ያላገኘው የሱዳን ጦር እና የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦርነት አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል።
የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች፣ አሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ ሁለት ወራት ያስቆጠረውን ጦርነት እንዲያቆሙ ያቀረቡትን ጥሪ ለመቀበል ብዙም ዝግጁ አይደሉም።
ጦርነቱ አሁን ላይ ተባብሶ ሀገሪቱን ወደ ከፋ ቀውስ ውስጥ አስገብቷታል።
የሱዳን ጦርም ሆነ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል
በጂዳ በነበረው ድርድር ተኩስ ለማቆም ተቸግረው ነበር፤ ይህም የሆነው በከፊል በቀጣናው ያሉ የተቀናቃኝ ኃይሎች እጅ ነው ሲሉ ዲፕሎማቶች ወቀሳ አቅርበዋል።
ሱዳን በአንድ ወቅት አጋር በነበሩት በሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አልቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ ጀነራል ሃምዳን ደጋሎ ወይም ሄሜቲ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ሁለት ወር አልፎታል።
የካርቱም ነዋሪዎች በምግብ እጥረት እና እየተስፋፋ በመጣው ዝርፊያ ምክንያት ከባድ ጊዜ እያሳለፉ ናቸው።
በጦርነቱ ሁለት ሚሊዮን ሱዳናውያን ከቀያያቸው ተፈናቅለዋል።
የጦርነቱ መቀስቀስ የቀድሞ ፕሬዝደንት አልበሽር በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ሀገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸጋገር ስታደርገው የነበረውን ጥረት አስተጓጉሏል።