ለመረጃ መንታፊዎች እንዳንጋለጥ ማድረግ ያሉብን ጥንቃቄዎች ምን ምን ናቸው?
ፌስቡክ ኩባንያ 2 ሚሊዮን ከመረጃ መንታፊዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው አካውንቶችን ዘግቷል
የመረጃ መንታፊዎች በዓመት 60 ቢሊዮን ዶላር እየመነተፉ ነው ተብሏል
ለመረጃ መንታፊዎች እንዳንጋለጥ ማድረግ ያሉብን ጥንቃቄዎች ምን ምን ናቸው?
የፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕ መተግበሪያዎች ባለንብረት የሆነው ሜታ ኩባንያ ከሰሞኑ በስሩ ባሉ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ተጠቃሚዎች መስለው ገንዘብ እና መረጃ መንታፊዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡
በተለይም ፌስቡክን ተጠቅመው አድብተው የተጠቃሚዎችን ገንዘብ ሲመትፉ ነበር ያላቸውን ከ2 ሚሊዮን በላይ አካውንቶችን እንደዘጋ ገልጿል፡፡
እንደ አሜሪካ ሰላም ኢንስቲትዩት ሪፖርት ከሆነ በዓመት 300 ሺህ የዓለማችን ዜጎች ለነዚህ መረጃ መንታፊዎች ተገደው ገንዘባቸውን ያስተላልፋሉ፡፡
እነዚህ መረጃ መንታፊዎች በየዓመቱ 60 ሺህ ዶላር ገቢ እያገኙ ነው የተባለ ሲሆን መንታፊዎቹ አሳሳች ማንነት ስለሚጠቀሙ ተጠያቂ ለማድረግ አስቸጋሪ ነውም ተብሏል፡፡
የደቡባዊ እስያ ሀገራት የሆኑት ምናማር፣ ላኦስ፣ ካምቦዲያ፣ ፊሊፒንስ፣ ታይላንድ፣ ቬትናም፣ ማሌዢያ እና ሌሎችም ሀገራት የመረጃ መንታፊዎች ዋነኛ መገኛ ሀገራት እንደሆኑ በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡
እነዚህ መንታፊዎች መጀመሪያ ላይ የሚያጠምዷቸውን ሰዎች በዘዴ ይለያሉ የተባለ ሲሆን ቀስ በቀስ ዕምነት እስከሚያገኙ ድረስ የተለያዩ ማታለያዎችን ይጠቀማሉ ተብሏል፡፡
ከዚያም ቀስ በቀስ የስራ እድል ማመቻቸት፣ መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም ገንዘብ መላክ፣ ገቢ እንዲያገኙ እድሎችን እስከ መፍጠር የሚያደርሱ ስራዎችን በማመቻቸት ይታወቃሉ፡፡
ከዚያም ቀስ በቀስ እምነት ካገኙ በኋላ የተሻለ ጥቅም ለማግኘት በሚል ሰብ ወዳዘጋጇቸው ወጥመዶች ቀስ በቀስ በመውሰድ ኢላማቸው ከተሳካ በኋላ አድራሻቸውን ሙሉ በሙሉ ያጠፋሉ፡፡
አሜሪካን 50 ቢሊየን ዶላር ያሳጡት አፍሪካውያን ዲጂታል አጭበርባሪዎች
ለመሆኑ ሰዎች በነዚህ መረጃ መንታፊዎች ሰላባ ላለመሆን ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄ ምንድን ነው?
የመጀመሪያው የጥንቃቄ እርምጃ የግል ወይም የስራ አካውንቶችን ጠንካራ እና አይገመቴ የይለፍ ቃል መጠቀም እንደሆነ ሜታ ኩባንያ ያወጣቸው የጥንቃቄ እርምጃ ሪፖርት ያስረዳል፡፡
ሁለተኛው ጥንቃቄ እርምጃ ከይለፍ ቃል በተጨማሪ ማንነቶን የሚያረጋግጡ እርምጃዎችን መከተል ሲሆን እንደ ግለምስል ወይም ሰልፊ ማረጋገጫ አይነት እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋልም ተብሏል፡፡
ታማኝ የመንግስት ተቋማት ሳይቀር የበይነ መረብ መንታፊዎች ሰላባ ሊሆኑ ስለሚችሉ ከመንግስት ተቋማት የተላኩ መልዕክቶችን በጥንቃቄ መመርመርም ያስፈልጋል፡፡
ካልታወቁ እና እምነት ከሌላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት የሚመጡ ጥቅማ ጥቅሞችን መጠራጠር ሌላኛው የጥንቃቄ እርምጃ ሲሆን የበይነ መረብ ማስታወቂያዎች እና ከሚያውቁት ሰው ሳይቀር የሚላኩ ሊንኮችን ቶሎ ከመክፈት መቆጠብ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡