በዛምቢያ የተካሄደውን ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የታቀዋሚ ፓርቲ መሪው ሂቺሊማ አሸንፈዋል
ተሰናባቹ የዛምቢያ ፕሬዘዳንት ለ60 ፍርደኛ እስረኞች ምህረት አደረጉ።
በደቡብዊ የአፍሪካ ክፍል የምትገኘው ዛምቢያ ባሳለፍነው ሳምንት ባካሄደችው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑት ሂቺሊማሸነፋቸው ይታወሳል።
በዚህ ምርጫ ላይ የተሸነፉት የወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ኤድጋር ሉንጉ ስልጣናቸውን ለአዲሱ ፕሬዘዳንት ከማስረከባቸው በፊት በእስር ላይ ላሉ ዜጎች ምህረት ማድረጋቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
ፕሬዘዳንቱ በሀገሪቱ የተለያዩ እስር ቤቶች ያሉ ነገር ግን ህመም ያለባቸው፤በእድሜ የገፉ፤ሴቶች እና በፖለቲካ ምክንያት ታስረው የነበሩ በድምሩ 60 እስረኞች በፕሬዘዳንቱ ምህረት ተደርጎላቸዋል ተብሏል።
ፕሬዘዳንቱ ለእስረኞቹ ምህረት ያደረጉት በዛምቢያ ህገ መንግስት መሰረት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በተለይም በፕሬዘዳንቱ ላይ ትችቶችን ይሰነዝሩ የነበሩ እስረኞች በምህረቱ እንዲፈቱ መደረጉ ብዙዎችን አስገርሟል ተብሏል።
በዛምቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ባሳለፍነው ሳምንት በ156 የምርጫ ክልሎች ድምጽ የተሰጠ ሲሆን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በ155 የምርጫ ክልሎች የተገኙ ደምጾችን መሰረት በማድረግ ውጤቱን ይፋ አድርገዋል፡፡
የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ኤሳው ቹሉ በተካሄድው ምረጫ ሂቺሊማ ከ50 በላይ ማለትም 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ድመጽ እንዲሁም ሉንጉ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን የሆነ ድምጽ አግኝተዋል።
የናጠጡ ባለሀብት እንደሆኑ የሚነገርላቸው የ59 ዓመቱ ሂቺሊማ ባለፉት አምስት ምርጫዎች ተሳትፈው ሳይሳካላቸው ቢቀርም አሁን ላይ አዲስ ፕሬዝዳንት በመሆን የሀገሪቱ በትረ ስልጣን መጨበጥ ችሏል፡፡
ሂቺሊማ በምርጫ ዘመቻ ሲሉት እንደነበር ሁሉ የዛምባያን ኢኮኖሚ ሪፎርም የማድረግ ከፍተኛ የቤት ሰራ እንደሚጠበቅባቸውም የአገሪቱ ፖለቲከኞች በመናገር ላይ ናቸው።