በዛምቢያ የተካሄደው ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ አልነበረም- የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት
ፕሬዚዳት ኤድጋር ሉንጉ በድመጽ አሰጣጡ ወቅት የፓርቲያቸው ተወካዮች ከምርጫ ጣቢያዎች መባረራውን ገልጸዋል
በምርጫው በስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉ በተፎካካሪያቸው ሀኬንዴ ሂችልማ እየተመሩ ይገኛሉ
የዛቢያው ፕሬዚዳት ኤድጋር ሉንጉ ሀገራቸው ባሳለፍነው ሀሙስ ያካሄደችው ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ አልነበረም ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
በዛምቢያ ፐሬዚዳንታዊ ምርጫ ጊዜያዊ ውጤት መሰረት የዛምቢያው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሀኬንዴ ሂችልማ ምርጫውን እየመሩ መሆኑ ተሰምቷል።
በምርጫው እየተመሩ ያሉት ፕሬዚዳት ኤድጋር ሉንጉ በምርጫው ወቅት የፓርቲያቸው የፓትሪዮቲክ ፍሮንት ተወካዮች እና ታዛቢዎች ከምርጫ ጣቢያዎች ላይ መባረራቸውን ገልጸው፤ ይህ ደግሞ የድምጽ አሰጠጥ ሂደቱን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ አድርጓል ብለዋል።
ለሁለተኛ ዙር ስልጣን ዘመን እየተወዳደሩ የሚገኙት ፕሬዚዳት ኤድጋር፤ በተሸነፉባቸው ስፍራዎች የተነሱ ሁከቶችም ተቀነባበሩ እንደመሆናቸው ገልጸዋል።
በዛምቢያ ደቡባው እና ሰሜን ምእራብ ግዛቶች ግጭቶች መቀስቀሳቸውንም ፐሬዚዳንቱ በመግለጫቸው ያነሱ ሲሆን፤ ሰሜን ምእራብ ግዛት ፓትሪዮቲክ ፍሮንት ፓርቲ አመራር መገደላቸውንም አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳት ኤድጋር ሉንጉ ፓርቲያቸው ፓትሪዮቲክ ፍሮንት ምርጫውን እና አመጹን በተመለከት ለሌላ የእርጃ ምእራፍ እየተዘጋጀ መሆኑንም አስታውቀዋል።
የምርጫውን ውጤት በመምራት ላይ የሚገኙት ተቃዋሚው ሀኬንዴ ሂችልማ በበኩላቸው፤ “ይህ የተሰናባቹ አስተዳደር የመጨረሻ ተግባር ነው” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
የዛምቢያ የምርጫ ኮሚሽን ከምርጫው ውጤት እና እየቀረቡ ስላሉ ቅሬታዎች እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።
በደቡባዊ አፍሪካ ክፍል የምትገኘው ዛምቢያ ባሳለፍነው ሀሙስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማካሄዷ ይታወቃል።
የመራጮች ድምጽ አሰጣጥ ሂደት መጠናቀቅን ተከትሎ ከትናነት ረፋድ ጀምሮ የምርጫ ውጤት በየምርጫ ጣቢያዎች በመለጠፍ ላይ ይገኛሉ።
የመራጮች ድምጽ ቆጠራ ምርጫው በተካሄደባቸው 156 ምርጫ ክልሎች ውስጥ እስካሁን በ15ቱ የመራጮች ድምጽ ቆጠራው ተጠናቆ ውጤት ይፋ ተደርጓል።
በተካሄዱ የድምጽ ቆጠራ ተቃዋሚው ሀኬንዴ ሂችልማ 171 ሺህ 604 ድምጽ ሲያገኙ በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዘዳነት ኤድጋር ሉንጉ በ110 ሺህ 178 ድምጾች እየተከተሉ እንገሚገኙ ተነግሯል።