ፕሬዘዳንት ሉንጉ ክስ እንዲያቀርቡ የተወሰኑ የፓርቲያቸው አባላት ጫና እንዳሳደሩባቸውም ግልጸዋል
ተሰናባቹ የዛምቢያ ፕሬዘዳንት ሉንጉ ባለፈው ሳምንት በሀገሪቱ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ለመቃወም ክስ እንደማያቀርቡ ተናግረዋል፡፡
በሚቀጥለው ሳምንት ስልጣን የሚረከቡት የተቃዋሚ መሪው ሃኬንዴ ሂቺሌማ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫውን ያሸነፉት ሉንጉን በ1ሚሊዮን የድምጽ ብልጫ መሆኑን ሲጂቲዜን ዘግቧል፡፡ ቀደም ሲል ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ አልነበረም ያሉት ፕሬዘዳንት ሉንጉ፤ በምርጫ ውጤቱ ላይ ክስ ማቅረብ ጊዜ ማባከን ስለሚሆን ክስ አላቀርብም ብለዋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ የተሰናቹ ገዥ ፓርቲ ፓትሪዎቲክ ፍሮንት ሁለት አባላት በሰሜዊ ምእራብ ክፍል በምትገኘው ሶልዊዝ ግዛት ስርአተ ቀብር በሚፈጸምጽ ጊዜ ባሰሙት ንግግር፣ የፓርቲያቸው አባላት ክስ እንያቀርቡ ግፊት ማሳደራቸውንና ጊዜ ማጥፋት ነው በሚል አለመቀበላቸውን ገልጸዋል፡፡
የተወሰኑ የፓርቴ አባላት ፍርድቤት ሄደው ክስ እንዲያቀርቡ ግፊት እያሳደሩባቸው መሆኑን የገለጹት ፕሬዘዳንቱ ክስ አንደማያቀርቡ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ እንዳሉት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ፤ በፈረንጆቹ 2016 ሂቺሌማ አቤቱታ ማቀረበት ወቅት ተፈጥሮ አንደነበረው አይነት አላስፈላጊ ውጥት እንዲፈጠል አልፈልግም ብለዋል፡፡