ፖለቲካ
የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ልጃቸውን ሚንስትር አድርገው መሾማቸው ቁጣን ቀሰቀሰ
ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ካቢኔያቸውን ሲያደራጁ ልጃቸውን ምክትል የፋይናንስ ሚንስትር አድርገዋል
ተቃዋሚዎች እርምጃዎችን 'የቤተሰቦች ሹመት' ብለውታል
የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ልጃቸውን ሚንስትር አድርገው ስልጣን መስጠታቸው የ'ቤተ ዘማድ' ሹመት በሚል አስተችቷቸዋል።
ፕሬዝዳንቱ ሰኞ ዕለት ዴቭድ ኩዳክዋሽ የተባለውን ልጃቸውን 'ለም/ቤት የወጣቶች ተዋጽኦ' በሚል ምክትል የፋይናንስ ሚንስትር አድርገው ሾመዋል።
የሀገሪቱ ብዙኸን መገናኛዎች እንደዘገቡት ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ሌላኛውን የቤተሰብ አባላቸውን (የእህታቸው/የወንድማቸው ልጅ) ምክትል የቱሪዝም ሚንስትር አድርገዋል።
ተቃዋሚዎች እርምጃዎችን የቤተሰቦች ሹመት ሲሉ ነቅፈውታል።
የማህበራዊ የትስስር ገጾች ተጠቃሚዎችም በሹመቱ ብስጭታቸውን ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
እስካሁን ድረስ ከገዥው ፓርቲም ሆነ ከመንግስት የተሰነዘረውን ትችት የሚያስተባብል ምላሽ አልተሰጠም።
ሆኖም የፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ደጋፊዎች ልጃቸው ለቦታው ብቁ መሆናቸውን በመግለጽ እየተከራከሩ ነው።
ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ያሸነፉበት የዚምባቡዌ ምርጫ ተቃዋሚዎች "ተጭበርብሯል" በሚል ክስ ቅቡልነት አላገኘም።
ታዛቢዎችም ምርጫው ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ መመዘኛዎችን ያሟላ አይደለም ብለዋል።ተቃዋሚዎች እርምጃዎችን 'የቤተሰቦች ሹመት' ብለውታል