ፖሊስ 33 እስረኞችን ሲገድል 15 እንዳቆሰለ ተገልጿል
በሞዛምቢክ ከ1 ሺህ 500 በላይ እስረኞች አመለጡ፡፡
በደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ሞዛምቢክ ከሁለት ወራት በፊት የተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አለመረጋጋት አስከትሏል፡፡
በተለይም የምርጫው አሸናፊ የገዢው ፓርቲ እጩ እንደሆኑ ከተገለጸ በኋላ በሀገሪቱ መዲና ሞፑቱን ጨምሮ በሌሎችም ዋና ዋና ከተሞች ለይ የፖለቲካ አለመረጋጋት አጋጥሟል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ደግሞ 1 ሺህ 500 እስረኞች ከማረሚያ ቤት አምልጠዋል የተባለ ሲሆን ፖሊስ ከ33 እስረኞችን ሲገድል 15 አቁስሏል ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም አምልጠው የነበሩ 150 እስረኞችን መልሶ በቁጥጥር ስር እንዳዋለም አስታውቋል፡፡
እስረኞቹ ያመለጡት ተቃዋሚዎች በእስር ቤቱ አቅራቢያ እየጮሁ እያለ ታራሚዎች ይን አጋጣሚ ተጠቅመው አምልጠዋ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ገዢው ፈሬሊሞ ፓርቲ ከ1975 ዓመት ጀምሮ በስልጣን ላይ ሲሆን የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የምርጫውን ውጤት ከሰሞኑ ማጽደቁን ተከትሎ ዳግም አለመረጋጋት ተከስቷል፡፡
የገዢው ፓርቲ ዋነኛ እጩ የሆኑት ዳንኤል ቻፖ ምርጫውን እንዳሸነፉ የተገለጸ ሲሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ተቃውሞ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
የሞዛምቢክ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ዳንዔል ቻፖ የመራጮችን 65 በመቶ ድምጽ አግኝተው አሸንፈዋል ሲል አጽድቋል፡፡
የፖለቲካ ቀውሱን ተከትሎ በሞፑቶ ባንኮች፣ የኝግድ መደብሮች እና መዝናኛ ቤቶች በገና በዓል ማግስት ተዘግተዋልም ተብሏል፡፡
ምርጫው ከተደረገበት ጥቅምት ወር ጀምሮ በአጠቃላይ 150 የሀገሪቱ ዜጎች እንደተገደሉ የፖሊስ ሪፖርት ያስረዳል፡፡