በዚህ ዓመት ብቻ በምሰራቅ አፍሪካ ከ260ሺ በላይ ህጻናት በረሃብ ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተገለጸ
ምስራቅ ኬንያ፣ደቡብ ሶማሊያ እና አንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተከታታይ ለድርቅ የሚጋለጡ አከባቢዎች ናቸው
በ2022 ተጨማሪ 3.6 ሚሊዮን ህጻናት በአለም ዙሪያ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት እንዳይጋለጡ ከወዲሁ ተሰግቷል
በምስራቅ አፍሪካ በዚህ ዓመት ብቻ ከ260ሺ በላይ የሚሆኑ ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት በከፍተኛ በረሃብ እና በተዛማጅ በሽታዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ የህፃናት አድን ድርጅት/ሴቭ ዚ ቺልድረን/ አዲስ ገልጿል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተጠናቀረውን መረጃ መሰረት በማድረግ፤ ሴቭ ዘ ችልድረን በምስራቅ አፍሪካ በሚገኙ ስምንት ሀገራት ላይ ባደረገው ግምገማ፤ ወደ 262 ሺ 500 የሚጠጉ ህጻናት የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸው እንደሆኑና በጥር እና ህዳር 2021 መካከል በነበሩ ጊዜያት ሞተው ሊሆኑ እንደሚችሉ አረጋግጧል።
- ተመድ ገንዘብ የዓለምን ረሃብ እንዴት እንደሚፈታ ካስረዳኝ የቴስላን አክሲዮን በመሸጥ ገንዘቡን አስጣለሁ- ኤሎን መስክ
- በትግራይ ከ1 ሚሊዬን ለሚልቁ ተጨማሪ ሰዎች ምግብ ለማቅረብ መቻሉን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ
ምስራቅ አፍሪካ በአሁኑ ጊዜ የአየር ንብረት ለውጥ አስከፊ ተፅእኖዎች እያጋጠሟት ሲሆን እንደ ድርቅ እና የጎርፍ መጥለቅለቅ ያሉ ድንገተኛ አደጋዎች ለጅምላ መፈናቀል እና ለከፍተኛ ረሃብ ምክንያት እንደሆኑ ይነገራል።
ምስራቅ ኬንያ፣ደቡብ ሶማሊያ እና አንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተከታታይ ለድርቅ የሚጋለጡ ሲሆን፤የደቡብ ሱዳን የተወሰነ ክፍል በየሶስት አመታት በሚዘንበው ያልተጠበቀ ዝናብ የውሃ መጥለቅለቅ የሚገጥመው አከባቢ ነው፡፡
በ2021 በከፍተኛ ደረጃ የተመጣጠነ ምግብ እጦት የሚሰቃዩ ህጻናት በ16 በመቶ ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ የህጻናት ጤና ጣቢያ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡
በጣም አስከፊ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አደገኛ የሆነው የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ነው መሆኑ ይታወቃል።
በአሁኑ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ በከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ካለባቸው ህጻናት ከግማሽ ያነሱ (46 በመቶ) ለበሽታው ህክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል። በአለም አቀፍ ደረጃ የተመጣጠነ ምግብ እጦት ከአምስት አመት በታች ካሉ ህጻናት ሞት ጋር የተያያዘ ነው፡፡
እንደፈረንጆቹ በ2020፤194 ሚሊዮን ህጻናት ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ጉዳት (በጣም አጭር እና በጣም ቀጭን መሆን) ደርሶባቿል፡፡
ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፈጣን እና ወሳኝ እርምጃ ካልተወሰደ በ 2022 ተጨማሪ 3.6 ሚሊዮን ህጻናት በአለም ዙሪያ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ይጋለጣሉ እና ተጨማሪ 13.6 ሚሊዮን ህጻናት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጽዕኖ ምክንያት ይባክናሉ።
ሴቭ ዘ ችልድረን ለጋሾች ለቤተሰቦች ሰብአዊ የገንዘብ እና የቫውቸር ዕርዳታ ቅድሚያ እንዲሰጡ እና በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተው የጥቃት አደጋ -በተለይ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ እንዲያተኩሩ አሳስቧል።
በተጨማሪም ዓለም አቀፋዊ ግጭቶችን በማስቆም፣ የአየር ንብረት ለውጥንና የምግብ ስርአቶችን በመዋጋት እንዲሁም የበለጠ መቋቋም የሚችሉ ስርዓቶችን እና ማህበረሰቦችን በመገንባት ወደፊት ተመሳሳይ አደጋዎችን መከላከል ይቻላልም ብሏል ድርጅቱ።