በአንድ ቀን ብቻ 1 ሺህ 295 ስደተኞች ዩናየትድ ኪንግደም ገቡ
የፈረንጆቹ 2022 ከገባ ወዲህ ባሉ ጊዜያት ብቻ ከ22ሺህ 600 በላይ ሰዎች ወደ ዩኬ መግባታቸውም አኃዞች ያሳያሉ
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ፤ በዩናይትድ ኪንግደም ከ44 ሺ በላይ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞቸ ይገኛሉ
በአንድ ቀን ብቻ 1 ሺህ 295 ስደተኞች ዩኬ መግባታቸው የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡
የውሃ ሰርጦችን አቋርጠው ወደ ሀገሪቱ የዘለቁት ስደተኞች በ27 ጀልባዎች ተጉዘው የመጡ እንደሆኑም ነው የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር ጊዜያዊ መረጃ የሚያመላክተው።
የስደተኞቹ ቁጥር እንደፈረንጆቹ ከ2018 ወዲህ በየቀኑ እየተስተዋሉ ካሉ አሃዞች ሁሉ የበለጠ መሆኑ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እንደፈረንጆቹ በ2022 ብቻ ከፈረንሳይ ተነስተው እንደ ታንኳ በመሳሰሉ ትናንሽ ጀልባዎች በመጠቀም በተጨናነቀ የመርከብ መንገዶችን ከተጓዙ በኋላ ከ 22ሺህ 600 በላይ ሰዎች ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መግባታቸውን አኃዞች የሚሳዩ ሲሆን ይህም ካለፉት አመታት ጋር ሲጻጸር የስደተኞች ቁጥር በእጅጉ የላቀ መሆኑ የሚያመላከት ነው ተብሏል ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ወደ ስልጣን ሲመጡ የህገ ወጥ ስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ ቃል በመግባት ነበር፡፡ ሆኖም ቁጥሩ በገቡት ቃል ልክ ከመቀነስ ይልቅ ስለመጨመሩ ይነገራል፡፡
በዩናይትድ ኪንግደም 44 ሺ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞቸ እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
የሩዋንዳው ስምምነት ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ጫና ለመቅለል በማሰብ የተደረገ እንደሆነም ነው የሚነገረው፡፡
የስደተኞችና የጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ ያንገበገባት ዩናይትድ ኪንግደም ከሩዋንዳ ጋር ጥገኝነት ጠያቂዎችን እና ስደተኞችን ለማስተናገድ የሚያስችል የሚልየን ዶላሮች ስምምነት ባሳለፍነው ወርሃ ሚያዝያ መፈራረሟ የሚታወስ ነው።
በተለያዩ ከህግ ጋር የተያየዙ ጉዳዮች ምክንያት ስምምነቱ ተግባራዊ ለማደረግ ቢዘገይም፤ ስምምነቱብ በተመለከተ በወቅቱ ተናገሩት የብሪታኒያ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ፕሪቲ ፓቴል ከሩዋንዳ ጋር የተደረሰው ስምምነት “ህገ ወጥ ስደትን ለማስቀረት የሚያግዝ ቁልፍ ስትራቴጂ ነው” ማለታቸው ይታወሳል፡፡፡