ብሪታኒያ በስደተኞች ላይ “ኤሌክትሮኒክ መለያ” ልትገጥም ነው
ቦሪስ ጆንሰን “ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደተቀረው የሀገሪቱ ክፍል መጥፋት እንደማይችሉ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው" ብለዋል
የብሪታኒያ እቅድ “ስደተኞችን እንደ ወንጀለኞች የሚመለከት ነው” በማለት በርካቶች እየተቹት ነው
ብሪታኒያከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ወደ ሀገሪቱ የገቡት ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች ለመቆጣጠር በሚል “የኤሌክትሮኒክ መለያ” ልትገጥም ነው፡፡
የኤሌክሮኒክ መለያው፤ የብሪታኒያ መንግስት አደገኛ በሚላቸው መንገዶች የገቡ ስደተኞች ለመለየትና አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል እንደሆነም የብሪታኒያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ሆኖም አሁን የብሪታኒያ መንግስት ሊተገብረው ያሰበው የኤልክትሮኒክ መለያ፤ በረራው በተሳካ ሁኔታ እንዳይሳካ የተሟገቱ የሆኑ ስደተኞች ላይ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ መሆኑም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
“መለያ የተገጠመላቸው ስደተኞች የሰዓት እላፊ ገደብ ሊጣልባቸው ይችላል እንዲሁም የተሰጧቸውን ትዕዛዞች የማያከብሩ ከሆነም ወደ እስር ቤት ሊወሰዱ ወይም ሊከሰሱ ይችላሉ”ም ተብሏል፡፡
ምንም እንኳን ሙከራው እንደተጀመረ ቢነገርም፤ የብሪታኒያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እስካሁን የኤሌክትሮኒክ መለያ ተገጥሟል ስለሚለው ምንም አይነት አስተያየት አልሰጠም ።
ቦሪስ ጆንሰን “ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደተቀረው የሀገሪቱ ክፍል መጥፋት እንደማይችሉ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።
ቦሪስ ጆንሰን ይህን ይበሉ እንጅ፤ የብሪታኒያ መንግስት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በጥገኝነት ጠያቂዎችና በስደተኞች ላይ እየተከተለ ያለው ፖሊሲ “ስደተኞችን እንደ ወንጀለኞች የሚመለከት ነው” በማለት በርካቶች እየተቹት ነው፡፡
ከስደተኞች ጋር የሚሰሩ ሰራተኞች “መሳሪያው በሰውዬው አእምሮአዊ ወይም አካላዊ ጤንነት ላይ ከባድ ጉዳት የሚያደርስ እንዳይሆን አለባቸው”ም ነው ያሉት ተቺዎቹ፡፡
ይህ ጅማሮ የመጣው ስደተኞችን ከብሪታኒያ ወደ ሩዋንዳ ለማጓጓዝ የተደረገው መጀመሪያ ሙከራ ሳይሳካ መቅረቱ ተከትሎ ነው፡፡
በሳለፍነው ሳምንት ሊደረግ ታቅዶ ነበረው በረራ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ጣልቃ በመግባቱ ምክንያት በመጨረሻዎቹ ሰዓታት መታገዱ የሚታወስ ነው፡፡
ብሪታኒያ ከሩዋንዳ ጋር በደረሰችነት የሚልዮን ዶላሮች ስምምነት መሰረት፤ በሀገሪቱ የሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች ጉዳያቸውን ሩዋንዳ ሆነው ይከታተሉ በሚል ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ አሳፍራ ለመላክ አቅዳ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኗ ይታወቃል፡፡