የደን ቃጠሎዎች የኦዞን መጠንን እንዴት ይጎዳሉ?
የኦዞን መጠን መሳሳት የሰው ልጆች ለቆዳ ካንሰር እና ሌሎች ህመሞች ይዳረጋሉ ተብሏል
ምድራችን ከፍተኛ ሙቀት እንድታስተናግድ እና የብዝሃ ህይወት ውድመትን የምታስተናግደው በኦዞን መሳሳት እና ሌሎች ምክንቶች እንደሆነ ይገለጻል
የደን ቃጠሎዎች የኦዞን መጠንን እንዴት ይጎዳሉ?
ዓለማችን በየጊው በሚከሰቱ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንት በየጊዜው የተለያዩ ጉዳቶችን እያስተናገደች ትገኛለች፡፡
ይህን ተከትሎም የተወሰኑ አካባቢዎች በድርቅ ሲጠቁ ቀሪዎቹ በጎርፍ አንዳንዶቹ ደግሞ በከፍተኛ ሙቀት እና እሳት አደጋዎች እየተፈተኑ ይገኛሉ፡፡
ኦዞን የተሰኘው የአካባቢ አየር ምጣኔው በማጣጣም የሚታወቅ ሲሆን በተለይም ከጸሀይ ብርሃን የሚመጣ ሙቀትን እና የምድር ላይ ቅዝቃዜን ሚዛን በመጠበቅም ይታወቃል፤፡
የአየር ንብረት ለውጥ ለግጭት እና ጦርነት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተገለጸ
በደኖች ላይ የሚፈጠሩ እሳት አደጋዎች ይህን የኦዞን ንጣፍን በመጉዳት ከባድ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲከሰት ዋነኛ ምክንት ሆኗል፡፡
ይህ ለከባቢ አየር ሚዛን መጠበቅ አስተዋጽኦ የሚያደርገው ኦዞን በዶነች ላይ ቃጠሎ ሲከሰቱ ከፍተኛ የጸሀይ ሀይል ወይም ሙቀት ወደ ምድር እንዲገባ በማድረግ ምድራችን ከፍተኛ ሙቀትን እንድታስተናግድ ምክንያት ይሆናል፡፡
እንዲሁም በደኖች ላይ የሚደርሱ ቃጠሎዎች በኦዞን ላይ የኬሚካል ውህደቶችን በመፍጠር ጎርፍ እና ከባድ አውሎንፋሶች እንዲፈጠሩ ያደርጋሉም ተብሏል፡፡
የኦዞን መሳሳት ከፍተኛ የጸሀይ ሀይል ወደ ምድር እንዲመጣ በማድረግ እንደ ካንሰር እና መሰል የሰው ልጆችን ጤና እንደሚጎዳ ተመራማሪዎች ተናግረዋል፤፡
እንዲሁም እጸዋት ተፈጥሯዊ ኡደታቸውን ጠብቀው እንዳይራቡ እና በሰው እና እንስሳት የምግብ ዋስትና ላይ ችግር ይፈጥራልም ተብሏል፡፡
እንዲሁም በምድር ላይ ያሉ ውሃማ አካላት ከፍተኛ ሙቀትን በማስተናገድ በውሃ ውስጥ የሚኖሩ ብዝሃ ህይወት በሙቀት ምክንት እንዲሞቱ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡