ፖኪስታን ኢራን የአየር ክልሏን ጥሳ ጥቃት እንዳደረሰችባት አስታወቀች
ጃይሽ አል አድል የተባለው ቡድን በፖኪስታን ድንበር አቅራቢያ በኢራን የጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል
እስላማባድ ክስተቱ "ከባድ ችግር የሚያስከትል" እና "በፍጹም ተቀባይነት የሌለው" ነው ስትል አስጠንቅቃለች
ፖኪስታን ኢራን የአየር ክልሏን ጥሳ ጥቃት እንዳደረሰችባት አስታወቀች።
የኢራን የመንግሰት ሚዲያ የጃይሽ አል አድል የተባለው ታጣቂ ቡድን ሁለት ካምፖች በሚሳይል መመታታቸውን ከገለጸ ከሰአታት በኋላ ፖኪስታን ጎረቤቷ ኢራን የአየር ክልሏን በመጣስ ሁለት ሰዎች እንደገደለችባት ገልጻለች።
የፖኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ቢሮ ባወጤው መግለጫ እስላማባድ ክስተቱ "ከባድ ችግር የሚያስከትል" እና "በፍጹም ተቀባይነት የሌለው" ነው ስትል አስጠንቅቃለች።
ባለፈው ሰኞ እለት የኢራኑ ሪቮሉሽናሪ ጋርድስ በኢራቅ እና በሶሪያ ያሉ ኢላማዎችን መትቷል።
ጃይሽ አል አድል በፖኪስታን ድንበር አቅራቢያ በኢራን የጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል።
"እነዚህ ካምፖች በሚሳይል እና በድሮን ወድመዋል" ሲሉ የኢራን ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ለሀገሪቱ ከፍተኛ ጸጥታ ኃይል ቅርብ የሆነው የኢራኑ ኖርኒውስ ጥቃት የደረሰባቸው ካምፖች በፖኪስታኗ ባሎችስታን ግዛት ውስጥ ይገኛሉ።
የፖኪስታኑ መግለጫ ቦታውን አልጠቀሰም፣ ነገርግን ቅሬታውን ለኢራቅ ማሰማቱን እና በእስላማባድ ያለውን የኢራን ልኡክ ኃላፊ ለማብራሪያ መጥራቱን ገልጿል።
ፖኪስታን ጥቃቱን ተከትሎ ለሚመጣው ችግር ኢራን ኃላፊነቱን እንደምትወስድ ገልጻለች።