በፓኪስታን የኢትዮጵያን ጨምሮ የ12 ሀገራት ዲፕሎማቶች ላይ ያነጣጠረ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ
በፓኪስታን በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 1 ፖሊስ ሲሞት 3 ሰዎች ቆስለዋል
ኢትዮጵያ አምባሳደሯን ጨምሮ የሌሎች ሀገራት ዲፕሎማቶች ላይ ያነጣጠረውን የሽብር ጥቃት አውግዛለች
በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ልዑኮችን ባካተተ የዲፕሎማቲክ ኮንቮይ ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙ ተነግሯል።
መንገድ ዳር በተጠመደ ቦምብ አማካኝነት በተፈጸመው የሽብር ጥቃት አንድ የፖሊስ አመራር ሲሞት፤ 3 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውም ነው የተነገረው።
ዲፕሎማቶቹ አፍጋኒስታን በሚያዋስነው በከይበር ፓክቱንክዋ ግዛት ወደሚገኝ የቱሪስት ስፍራ እየተጓዙ እያለ የሽብር ጥቃቱ መፈጸሙም ተነግሯል።
የዲፕሎማቲክ ኮንቮይው በስዋት አካባቢ በሚገኝ በማላም ጃባባ የቱሪስት ቦታ እና ኮረብታ ጣቢያ በማለፍ ላይ እያለ ቀድሞ መንገድ ዳር በተቀበረ ቦምብ ጥቃት እንደተፈጸመበትተጠቅሷል።
የስዋት አካባ ፖሊስ አዛዥ ዛሂዱላህ ካን በቦምብ ጥቃቱ “አንድ ፖሊስ ህይወቱ ሲያልፍ ሌሎች ሶስት ፖሊሶች ደግሞ ቅስለዋል ብለዋል።
ዲፕሎማቶቹ በፖሊስ መኪና እየተመሩ ሲጓዙ እንደነበረ የገለጹት የፖሊስ አዛዡ፤ በጥቃቱ ጉዳት የደረሰበት መንገድ እየረመራ የነበረው የፖሊስ መኪና እንደሆነ አስታውቀዋል።
ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም ተብሏል።
የዲፕሎማቲክ ኮንቮይ ውስጥ የነበሩ ዲፕማች የየት ሀገራት ናቸው?
የሽብር ጥቃት የተፈጸመበት የዲፕሎማቲክ ኮንቮይ ውስጥ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በኽርን ጨምሮ የኢንዶኔዢያ፣ የፖርቹጋል፣ የካዛኪስታን፣ የቦስኒያና ሄርዞጎቪና፣ ዚምባቡዌ፣ ሩዋንዳ፣ ቱርከምንስታን፣ ቬትናም፣ ኢራን፣ ሩሲያ እና ታጃኪስታን አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ናቸው።
ሁሉም ዲፕሎማቶች በጥቃቱ ምንም ዓይነት አደጋ ሳይደርስባቸው ወደ ዋና ከተማዋ ኢዝላማባድ በሰላም እንደተመለሱ ፖሊስ አስታውቋል።
የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻዝ ሻሪፍ እና ፕሬዝዳንት አሲፍ አሊ ዛርዳሪ ጥቃን ያወገዙ ሲሆን፤ በጥቃቱ ህይወቱ ላለፈው የፖሊስ አባል ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ በሌሎች የዲፕሎማቲክ ኮንቮይ ላይ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አውግዟል
ዲፕሎማቶቹን ሲያጅብ ለነበረው የሟች ፖሊስ ቤተሰብም መጽናናትን ተመኝታለች፡፡
የሽብር ጥቃቱን በጽኑ ያወገዘችው ኢትዮጵ፤ ለፓኪስታን ሕዝብና መንግሥትም መጽናናትን መመኘቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።